ማክተር ኩባንያ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ መዋዕለ ንዋይ ማፍሰስ እንደሚፈልግ ገለጸ

ማክተር የተሰኘው የፓኪስታን ኩባንያ በቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክ በፋርማሲዩቲካል ዘርፍ መዋዕለ ንዋይ የማፍሰስ ፍላጎት እንዳለው ገለጸ።

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ከማክተር ኩባንያ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሻህናዋዝ ሳጂድ ጋር ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም÷መንግስት ለፋርማሲዩቲካል ዘርፍ የሰጠውን ትኩረት፣ ኮርፖሬሽኑ ያቀረባቸውን ዘርፈ ብዙ ማበረታቻዎችና ያለውን የተሟላ መሰረተ ልማት አስረድተዋል።

በሌላ በኩል ዶ/ር ሻህናዋዝ ሳጂድ የቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርክን መሰረተ ልማትና ወቅታዊ የምርት እንቅስቃሴ ሒደት ጎብኝተዋል።

ማክተር ኢንተርናሽናል መቀመጫውን ፓኪስታን ያደረገ ከ40 ዓመታት በላይ ልምድ ያለው የፋርማሲዩቲካል ግዙፍ ኩባንያ መሆኑ ተገልጿል።

ከዓለም አቀፍ አጋሮች ጋር በመስራት ምርቱን በእስያ፣ በአፍሪካ፣ በተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች እና በሌሎች የዓለም ሀገራት በማከፋፈል ላይ እንደሚገኝም የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *