የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ወደ ጓንዡ ከተማ የመንገደኞች በረራ ማድረግ የጀመረበትን 20ኛ ዓመት አክብሯል።
ዓየር መንገዱ ወደ ከተማዋ የመንገደኞች በረራ የጀመረው ሕዳር 17 ቀን 1996 ዓ.ም መሆኑ ተገልጿል።
በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ወደ ጓንዡ በሣምንት 10 የመንገደኞች በረራ እያደረገ መሆኑም ተጠቁሟል።
ዓየር መንገዱ በቻይና 10 የዕቃ ጭነት (ካርጎ) እና የመንገደኞች በረራ መዳረሻዎች እንዳሉትም ነው የተገለጸው።
በቅርቡም ወደ ቻይና በረራ ማድረግ የጀመረበትን 50ኛ ዓመት በድምቀት ማክበሩ ከኢትዮጵያ ዓየር መመንገድ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።