አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1/ 2015
የእስያ ሀገራት ያላቸውን ግንኙነት አጠናክረው የሚቀጥሉ ከሆነ በዓለም የሚፈጠሩ አዳዲስ ለውጦችን በቀላሉ መቋቋም እንደሚችሉ የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ችያንግ ተናገሩ፡፡
26ኛው የቻይና -ኤስያ የመሪዎች ጉባኤ በኢንዶኖዥያ ጃካርታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡
በጉባኤው የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ችያንግ፣ የቻይናና የሌሎች የእስያ ሀገራት ትብብር በብዙ አስቸጋሪ ጊዜያት ሳያናወጥ ለረጅም ጊዜ መቆየት መቻሉን አንስተዋል፡፡
ቻይናን ጨምሮ የእስያ ሀገራት አህጉራዊ ሰላምና ልማትን ለማስፈን እንደሚሰሩ ተናግረው፤ ሀገራቱ ያላቸውን ግንኙነት አጠናክረው የሚቀጥሉ ከሆነ በዓለም የሚፈጠሩ አዳዲስ ለውጦችን በቀላሉ መቋቋም ይችላሉ ብለዋል፡፡
ቻይና እና የኤስያ ሀገራት ጠንካራ የልማት ፍላጎት እንዳላቸው የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ሀገራቱ በእስያ ቀጠና ሰላም እና ልማትን ለማሰፈን ይሰራሉ ብለዋል፡፡
ሁለተኛ ቀኑን በያዘው 26ኛው የእስያ-ቻይና የመሪዎች ጉባኤ አህጉራዊ እድገትና የወደፊት የትብብር ሂደትን በተመለከተ ውይይት እየተደረገ መሆኑን ሲጂቲኤን ዘግቧል፡፡
ምንጭ፦ ሲጂቲኤን