የኢትዮጵያ የገንዘብ ሪፖርት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ

849 ሚሊዮን ዶላሩ በብድር መልክ የተገኘ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል

የገንዘብ ሚኒስቴር በበጀት ዓመቱ የዘጠኝ ወራት እቅዱን ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል።

ሚኒስቴሩ ባቀረበው የፋይናንስ ሪፖርቱ ላይ እንዳለው ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ ከብድር እና እርዳታ 4 ነትብ 5 ቢሊዮን ዶላር ተገኝቷል ብሏል።

ከተገኘው ከዚህ ውስጥ 54 በመቶው ዕርዳታ ነው የተባለ ሲሆን 849 ሚሊዮን ዶላር በብድር የተገኘ እንደሆነ ተገልጿል።

ከተገኘው ገቢ ውስጥም የዓለም ባንክ አንድ ቢሊዮን ዶላር ወደ ኢትዮጵያ ፈሰስ አድርጓል የተባለ ሲሆን ኢትዮጵያ ከዓለም ባንክ ጋር መልካም ግንኙነት እንዳላትም አስታውቃለች።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *