በኮምሽነር ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ የተመራ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮምሽን የፕሮሞሽን ቡድን በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት በመዘዋወር የሀገራችንን ዘርፈ ብዙ የኢንቨስትመንት ዕድል እና አማራጮችን ለተለያዩ አምራች ኢንደስትሪዎች እና ባለሀብቶች በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል። ቡድኑ በቆይታው ከ20 በላይ ሰመ ጥር የአውሮፓ አምራች ኩባንያዎችን በማግኘት በተለይም በግብርና እና ግብርና ማቀነባበሪያው የኢንቨስትመንት ዘርፍ ያሉ ዕድል እና አማራጮችን የማስተዋወቅ እና ግንዛቤ የማስጨበጥ ሰራን በመስራት ለይ ይገኛል።
የግብርናው ዘርፍ ለሀገራችን ኢኮኖሚ ቁልፍ ከሚባሉ ዘርፎች ዋነኛው እንደመሆኑ በዘርፉ ያሉ በተለይም በአትክልት እና ፍራፍሬ፣ የቅባት አህሎች፣ የእንስሳት ዕርባታ፣ ወተት እና የወተት ተዋዕጾ እና የተለያዩ እህሎችን የማቀነባበር ስራዎች ላይ በማተኮር በኢንቨስትመንት ዘርፉ ባላሀብቶች እንዲሳተፉ እና አለም አቀፋዊ የገበያ ትስስር እንዲፈጠር ቡድኑ ሰፊ የፕሮሞሽን ስራን በመስራት ላይ ይገኛል።
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን