የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከጉዋንዡ ባዩን ዓለም አቀፍ አየር መንገድ እውቅና ተበረከተለት

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከጉዋንዡ ባዩን ዓለም አቀፍ አየር መንገድ ጋር ባለው ጥብቅ የስራ ግንኙነት በአየር መንገዱ የሚዘጋጀው የቅርብ ትብብር ሽልማት ተበርክቶለታል።

እውቅናው የሁለቱን አየር መንገዶች ጠንካራ የስራ አጋርነት እንደሚያመላክትና የሚሰጠውን አገልግሎት የበለጠ ለማጠናከር እንደሚያግዘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ አሁን ላይ ከጉዋንዡ ባዩን ዓለም አቀፍ አየር መንገድ በሳምንት አስር በረራዎችን እንደሚያከናውን ገልጾ በአየር መንገዱ የሚሰጣቸውን አገልግሎቶች ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኑንም ገልጿል።

ለሁለቱ አየር መንገዶች የስራ ግንኙነት መጠናከር የጉዋንዡ ባዩን ዓለም አቀፍ አየር መንገድ ለሚያደርገው ቀጣይነት ያለው ድጋፍ አየር መንገዱ እያመሰገነ በቀጣይም ትብብራቸውን ለማጠናከር እንደሚሰሩ ያለውን እምነት አስታውቋል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *