የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ለኢትዮጵያ ዜጎች ቪዛ አሰጣጥ ላይ ገደብ መጣሉን አስታወቀ
ህብረቱ መደበኛው ቪዛ ለማግኘት የሚጠበቀው የ15 ቀን ጊዜ ወደ 45 ቀን አራዝሞታል
የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ቪዛ የመስጠትን ሂደት ላይ ጊዜያው ገደቦችን ማስቀመጡን በዛሬው እለት አስታውቋል።
ህብረቱ በዛሬው እለት በሳለፈው ውሳኔ የህብረቱ ለአባል ሃገራት ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያውያን ቪዛ አመልካቾች ቪዛ ሲፈልጉ ሊያሟ ይገባቸዋል ያላቸውን መስፈርቶችም አስቀምጧል።
- ኢትዮጵያውያን ያለ ቪዛ በፓስፖርት ብቻ መግባት የሚችሉባቸው ሀገራት የትኞቹ ናቸው?
- አሜሪካ በሀገሯ በጊዜያዊነት ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ተጨማሪ የመኖሪያ ጊዜ ፈቀደች
በዚህም ኢትዮጵያውያን የአውሮፓ ሀገራት ቪዛን ለማግኘት አስፈላጊ ሰነዶችን እንዲያቀርቡ እና በአውሮፓ ህብረት ህግ የተቀመጠውን መደበኛ መስፈርቶች እንዲያሟሉ ይገደዳሉ ተብሏል።
በተጨማሪም የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገራት ከሁለት ጊዜ በላይ ወደ አውሮፓ ሀገራት ለመግባት የሚያስችለውን ቪዛ ለኢትዮጵያውያን መስጠት አይችሉም ሲልም ከልክሏል።
ለዲፕሎማቲክ እና ለአገልግሎት ፓስፖርቶች የቪዛ ክፍያን በተመለከተም ኢትዮጵያውያን ቪዛ ሲፈልጉ መደበኛውን የቪዛ ክፍያ ለመክፈል ይገደዳሉ ብሏል ህብረቱ።
መደበኛው ቪዛ ለማግኘት የሚጠበቀው የ15 ቀን ጊዜ ወደ 45 ቀን መራዘሙንም የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት በመግለጫው አመላክቷል።
የቪዛ ገደቡ በኢትዮጵያውያን ዜጎች ላይ እንዲተላለፍ ምክንያት የሆነውም ህብረቱ “ከኢትዮጵያ መንግስት በቂ ትብብር እያገኘሁ አይደለሁም” የሚል ነው።
የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ኢትዮጵያ በህገ-ወጥ መንገድ በአውሮፓ ህብረት የሚቆዩ ዜጎቿን በማስመለስ ረገድ የምታደርገው ጥረት በቂ ባለመሆኑ የቪዛ ገደብ ውሳኔውን ማሳለፉንም አስታውቋል
ውሳኔው ለምን ያክል ግዜ እንደሚቆይ የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ያለው ነገር የለም።
አል ዐይን