የባንኩ አጠቃላይ ኃብት 1 ነጥብ 9 ትሪሊየን ብር ደረሰ

 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጠቃላይ ኃብት 1 ነጥብ 9 ትሪሊየን ብር መድረሱን የባንኩ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ ገለጹ።

የባንኩ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ÷ ቀደም ሲል ባንኩ ለትላልቅ ፕሮጀክቶች ግንባታ ቢሊየን ብሮችን በዝቅተኛ የወለድ ምጣኔ ሲያበድር በመቆየቱ ባንኩ ላይ የህልውና አደጋ ተጋርጦ እንደነበር አንስተው አሁን በተደረጉ ማሻሻያዎች የላቀ ሽግግርና ስኬት ላይ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህ ረገድ በቅርቡ ተግባራዊ የተደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ የባንኩን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ወደ ላቀ ምእራፍ ያሸጋገረ መሆኑን አብራርተዋል።
ባንኩ አሁን ላይ በሁሉም ረገድ ጥሩ ቁመና ላይ መሆኑን ጠቅሰው፥ በቀጣይም በተፈጠረው ምቹ ሁኔታ ጠንካራና ተወዳዳሪ በማድረግ ትርፋማነቱን ለማሳደግ የሚሰራ መሆኑን አረጋግጠዋል።

የባንኩ አጠቃላይ ኃብት አሁን ላይ 1 ነጥብ 9 ትሪሊየን ብር እንዲሁም አጠቃላይ ቁጠባው 1 ነጥብ 4 ትሪሊየን ብር ደርሷል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

በገበያ ላይ የተመሰረተ የውጭ ምንዛሬ አስተዳደር ስርአት ባንኩ ከውጭ ምንዛሬ ግኝት ባለፈ በቁጠባ ከፍተኛ እድገት እንዲያስመዘግብ እንዳስቻለው ተናግረው በዚህም በበጀት ዓመቱ እስካሁን 217 ቢሊየን ብር በቁጠባ መሰብሰብ መቻሉን ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *