ባለስልጣኑ ባወጣው መመሪያ የወጪ ደረጃ ያለውን ቡና በአገር ውስጥ መሸጥ የሚያስችል ሲሆን ሆኖም ግብይቱ ተቀባይነት ባለው የውጭ ምንዛሬ ብቻ ማድረግ የሚያስገድድ ነው።
ስለመመሪያው ካፒታል ያናራቸው እሴት የተጨመረበት ቡና ላኪዎች የባለስልጣኑ ውሳኔ ስር ነቀል እና ለአገር ኢኮኖሚ ከፍተኛ ፋይዳ የሚኖረው ነው ሲሉ አሞካሽተውታል።
እንደላኪዎቹ ገለፃ በኢትዮጵያ ከፍተኛ የውጪ ማህበረሰብ ቢገኝም ቀደም ሲል በነበረው ፖሊሲ የጥራት ደረጃው በወጪ ንግድ ደረጃ ያለን የኢትዮጵያን ቡና በአገሪቱ የሚኖሩ የውጭ ዜጎች ከውጭ እንዲያስገቡ ያሰውገድድ ነበር ብለው።
ምንጭ፦ ካፒታል