ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል በቻይና የሕዝብ ደኅንነት ሚኒስቴር የአለም ዓቀፍ ትብብር ዲፓርትመንት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኮሚሽነር ዣሃውይ ዦው ጋር ተወያዩ::

(ኢ ፕ ድ)
የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ክቡር ኮሚሽነር ጀነራል ደመላሽ ገ/ሚካኤል፤ የወቅቱ የምስራቅ አፍሪካ ፖሊስ አዛዦች ኅብረት ድርጅት ፕሬዚዳንት በቻይና የሕዝብ ደኅንነት ሚኒስቴር የአለም ዓቀፍ ትብብር ዲፓርትመንት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኮሚሽነር ዣሃውይ ዦው የተመራውን ልዑካን ቡድን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
እ.ኤ.አ ጁላይ 10 ቀን 2023 የቻይና የሕዝብ ደኅንነት ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ያደረጉትን ስምምነት ለማስቀጠል መክረዋል።
የቻይና የሕዝብ ደኅንነት ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የፎረንሲክ አቅምን ለማሳደግ በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ እየተገነባ የሚገኘውን የፎረንሲክ ልህቀት ማዕከልን በግብዓትና በሥልጠና ድጋፍ እንደሚያደርግ ከስምምነት ደርሰዋል።
በክቡር ኮሚሽነር ዣሃውይ ዦው የተመራው የልዑካን ቡድን ወደ ሀገራችን የመጣው ኮሚሽነር ጀነራል ጋባዥነት ሲሆን በዛሬው ዕለት የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዋና መሥሪያ ቤትና የፎረንሲክ ምርመራ ማዕከልን ጎብኝቷል።
በቀጣይ በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ እየተገነባ የሚገኘውን የፎረንሲክ ልህቀት ማዕከልን እንደሚጎበኝ ይጠበቃል።
መስከረም 3 ቀን 2016 ዓ.ም

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *