ከ590 ሚሊየን ዶላር በላይ ኢንቨስትመንት መሳብ መቻሉ ተገለጸ

ባለፉት 6 ወራት 597 ሚሊየን ዶላር በላይ ኢንቨስትመንት ያስመዘገቡ ባለሃብቶች ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና ድሬዳዋ ነጻ የንግድ ቀጣና መግባታቸውን የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታውቋል።

የኮርፖሬሽኑ የኢንቨስትመንት ፕሮሞሽንና ማርኬቲንግ ስራ አስፈጻሚ አቶ ዘመን ጁነዲ÷ ከ80 በላይ የተለያዩ ኢንቨስትመንቶች ኮርፖሬሽኑ ወደ ሚያስተዳድራቸው ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች መሳባቸውን ገልጸዋል።

በተሳቡት ኢንቨስትመንቶች 14 የማምረቻ ሼዶችና ከ70 ሄክታር በላይ የለማ መሬት ለባለሃብቶች መተላለፋቸውን አንስተዋል።

ኢንቨስትመንቶቹ በመቐለ፣ ቦሌ ለሚ፣ ቂሊንጦ፣ ኮምቦልቻ፣ ድሬዳዋ ልዩ ነፃ ንግድ ቀጠና፣ ጅማና ሰመራ ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች ውስጥ የሚሰማሩ መሆናቸውን የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *