ኢትዮጵያ ከጃፓን ጋር በንግድ መስክ ያላትን ትብብር ለማጠናከር የሚያስችል ስራ እያከናወነች ነው

ኢትዮጵያ ከጃፓን ጋር በንግድ እና ኢንቨስትመንት መስክ ያላትን ትብብር ለማጠናከር የሚያስችል ስራ እያከናወነች እንደምትገኝ በጃፓን የኢትዮጵያ አምባሳደር ዳባ ደበሌ ገለጹ።

አምባሳደር ዳባ በጃፓን በአልባሳት እና በተለያዩ ምርቶች የጅምላ ንግድ ላይ ከተሰማራው “KYO-ROMAN GROUP HOLDINGS” ኩባንያ የስራ ኃላፊዎች ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።

አምባሳደር ዳባ፥ ለአመራሮቹ የኢትዮጵያ የንግድ እድሎች እና አማራጮችን አስመልክቶ ገለፃ አድርገዋል።

ኢትዮጵያና ጃፓን አኩሪ የባህል ባለቤቶች መሆናቸውን ገልጸው፥ በቶኪዮ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የአገራቱን የህዝብ-ለህዝብ፣ የንግድ እና ኢንቨስትመንት ትብብር ለማጠናከር እየሰራ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

የካምፓኒው የስራ ኃላፊዎች የኢትዮጵያ የኦፓል ማዕድን ተቀባይነቱ ከፍ ያለ መሆኑን ገልጸው፥ ምርቱን ወደ ጃፓን በስፋት የማስገባት ፍላጎት አለን ብለዋል።

ኩባንያው እ.አ.አ በጁን ወር 2025 መጀመሪያ አካባቢ 40ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን ሲያከብር የኢትዮጵያን ኦፓል ማዕድን እንደሚያስተዋውቅ መግለጻቸውን በቶኪዮ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *