ኢትዮጵያ በኬንያ ናይሮቢ እየተካሄደ በሚገኘው አምስተኛው የጀርመን-አፍሪካ የንግድ ጉባዔ ላይ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ትገኛለች።
በጉባዔው ላይ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ ኢትዮጵያን ወክለው እየተሳተፉ ይገኛሉ።
የኬንያ የውጭ እና ዳያስፖራ ጉዳዮች ሚኒስትር ሙሳሊያ ሙዳቫዲ(ዶ/ር)፣ የጀርመን ምክትል መራሔ መንግስት ሮበርት ሀቤክ(ዶ/ር)፣ የአፍሪካ ሀገራት ልዑካን እና የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች በጉባዔው ላይ ታድመዋል።
የጀርመን የልማት ትብብር ተቋም(GIZ) ያዘጋጀው ይህ የንግድ ጉባዔ ጀርመን በአጠቃላይ አውሮፓን ከአፍሪካ ጋር በኢኮኖሚና በንግድ የማስተሳሰርና የማገናኘት አላማ እንዳለው ተገልጿል።
ጉባዔው እስከ ነገ እንደሚቆይ በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመለክታል።
ምንጭ፦ ኢዜአ