የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከጥቅምት 5 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ሱዳኗ የወደብ ከተማ ፖርት ሱዳን ዕለታዊ በረራ እንደሚጀምር አስታውቋል።
አየር መንገዱ ወደ ፖርት ሱዳን በረራ መጀመሩ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሀገራት ያላትን የመዳረሻ ቁጥር የበለጠ እንደሚያሰፋው ተጠቁሟል።
በተጨማሪም ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር ያላትን የንግድና ቱሪዝም ትስስር በማጎልበት የቀጣናውን የኢኮኖሚ እድገት የበለጠ እንደሚጠናክር መገለጹን የአየር መንገዱ መረጃ ያመላክታል።
ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ