አሥተዳደሩ ከ111 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሰበሰበ

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ ሥድስት ወራት ከ111 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን አስታወቀ።

የአሥተዳደሩ ምክር ቤት መደበኛ ጉባዔ ላይ የግማሽ ዓመቱን አፈጻጸም ሪፖርት እያቀረቡ ያሉት ከንቲባ አዳነች አቤቤ÷ 125 ነጥብ 5 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 111 ነጥብ 5 ተሰብስቧል ብለዋል።

አፈጻጸሙ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸርም የ37 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ብልጫ አሳይቷል ነው ያሉት።

የገቢና ወጪ መጣጣም ብሎም እድገቱ ከተማዋ ምን ያህል በፈጣን ለውጥ ውስጥ እንደሆነች ተጨባጭ ማሳያ ነው ሲሉም ተናግረዋል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *