ባንኮች 1 የአሜሪካ ዶላርን በስንት ብር እየመነዘሩ ነው?

የግል ንግድ ባንኮች ለአንድ ዶላር እስከ 124 ብር መግዣ እስከ 127 ብር መሸጫ ዋጋ አቅርበዋል

ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ተመን ይፋ ሲያደርግ በዶላር መግዣ ዋጋው ላይ የአንድ ብር ጭማሪ አድርጓል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ123.5986 ብር እየገዛ በ126.0706 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።

ዳሽን ባንክ ከሶስት ሳምንት በፊት ያወጣውን ተመን አስቀጥሏል። በዚህም አንድ ዶላርን በ124.7171 ብር እየገዛ በ127.2114 ብር እየሸጠ መሆኑን ገልጿል።

አቢሲኒያ ባንክ በውጭ ምንዛሬ ተመኑ ላይ መጠነኛ የሳንቲም ጭማሪ አድርጎ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.7045 ብር ገዝቶ በ127.1986 ብር እየሸጠ ነው።

ብርሃን ባንክ የምንዛሬ ተመኑ ላይ መጠነኛ የሳንቲም ጭማሪ አድርጓል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.8045 ብር ገዝቶ በ127.3006 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።

ጸደይ ባንክም የታህሳስ 14 የውጭ ምንዛሬ ተመኑ ላይ መጠነኛ ጭማሪ አድርጎ አንድ ዶላርን በ124.7440 ብር እየገዛ በ127.2389 ብር እየሸጠ መሆኑን ነው የገለጸው።

ጎህ ቤቶች ባንክ ከ20 ቀናት በፊት ያወጣውን የምንዛሬ ተመን አስቀጥሏል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.8705 ብር በመግዛት በ127.3679 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።

ምንጭ፦ አል አይን

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *