በአፋር ክልል ባለፉት ስድስት ወራት ከ2 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የክልሉ የገቢዎች ቢሮ አስታወቀ።
የገቢዎች ቢሮ ኃላፊው አቶ አወል አብዱ ገቢው የተሰበሰበው በስድስት ወራት ውስጥ ለመሰብሰብ ከታቀደው 2 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ውስጥ መሆኑን ገልፀዋል።
ይህም የዕቅዱን 97 በመቶ ማሳካት መቻሉን አመልክተዋል።
ገቢው ከባለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጻር የ42 በመቶ ብልጫ እንዳለው ከክልሉ ገቢዎች ቢሮ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ምንጭ፦ ኢዜአ