በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኢትዮ-ኮሪያ ቴክስታይል ቴክኖ ፓርክ ፕሮጀክት ተመረቀ

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኢትዮ-ኮሪያ ቴክስታይል ቴክኖ ፓርክ ፕሮጀክት በዛሬው ዕለት ተመርቋልበምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ እና በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ካንግ ሴኪዮሄ ተገኝተዋል። አቶ አክሊሉ ታደሰ÷ ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ በደምና አጥንት የተሳሰረ ረጅም ዓመት የዘለቀ ጠንካራ ግንኙነት ያላቸው ሀገራት መሆናቸውን አውስተዋል።

ይህ ግንኙነት በመሰል ፕሮጀክቶች መጠናከሩ ለቀጣይ ግንኙነት ግብዓት መሆኑን ነው የተናገሩት።ደቡብ ኮሪያ በዘርፉ የደረሰችበትን ውጤታማነት በኢትዮጵያ በአጭር ጊዜ እውን ለማድረግ ፕሮጀክቱ ያለው ሚና ጉልህ መሆኑን ጠቁመው÷ ሌሎች ፕሮጀክቶች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ በትብብር ይሰራል ብለዋል።

አምባሳደር ካንግ ሴኪዮሄ በበኩላቸው÷ የቴክኖ ፓርክ ፕሮጀክት ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ ያላቸውን ግንኙነት የሚያጠናክርና የወደፊት የአብሮነት ጉዞ ማሳያ መሆኑን ገልፀዋል።ደቡብ ኮሪያ በሌሎችም ዘርፎች ከኢትዮጵያ ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆኗን እንዳረጋገጡ የኮርፖሬሽኑ መረጃ ያመላክታል

በቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ የሚገኘው የኢትዮ-ኮሪያ ቴክስታይል ቴክኖ ፓርክ በኢንዱስትሪ ፓርኮች የሚመረቱ የቴክስታይል ምርቶች የሚፈተሹበት፣ ዲዛይን ላይ ለሰራተኞች የተግባርና ቴክኒካል ስልጠና የሚሰጥበት መሆኑ ተገልጿል።

ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

 

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *