በታህሳስ 21 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን ዶላር በስንት ብር እየተመነዘረ ነው?

የግል ንግድ ባንኮች ለአንድ ዶላር ከ124 ብር ጀምሮ የመግዣ ዋጋ አቅርበዋል

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1 ዶላርን በ123 ብር ገዝቶ በ126 ብር እንደሚሸጥ አስታውቋል

ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ታህሳስ 21 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ተመን ይፋ ሲያደርግ የባለፈውን ሳምንት ዋጋ አስቀጥሏል። ባንኩ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ123.5986 ብር እየገዛ በ126.0706 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።

ዳሽን ባንክ ከአንድ ወር በፊት በፊት ያወጣውን ተመን ያስቀጠለ ሲሆን አንድ ዶላርን በ124.7171 ብር በመግዛት በ127.2114 ብር እየሸጠ ይገኛል።

አቢሲኒያ ባንክ ከአራት ቀናት በፊት ያወጣውን የምንዛሬ ተመን አስቀጥሏል። በዚህም አንድ ዶላርን በ124.7045 ብር እየሸጠ በ127.1986 ብር እየሸጠ እንደሚገኝ ገልጿል።

ብርሃን ባንክ የምንዛሬ ተመኑ ላይ መጠነኛ የሳንቲም ጭማሪ አድርጎ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.8075 ብር ገዝቶ በ127.3037 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።

ኦሮሚያ ባንክ የታህሳስ 21 2017 የውጭ የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ124.7099 ብር ገዝቶ በ127.2041 ብር እየሸጠ መሆኑን ጠቁሟል።

ምንጭ፦ አል አይን

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *