ከ1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በሚልቅ ወጪ የተገነቡ ፋብሪካዎች ሥራ ጀመሩ
በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከ1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በሚልቅ ወጪ የተገነቡ ፋብሪካዎች ተመርቀው ወደ ምርት መግባታቸው ተገለጸ፡፡ “የኢትዮጵያ ታምርት፣ እኛም እንሸምት” 3ኛ ዙር ንቅናቄ በድሬዳዋ ከተማ ተጀምሯል፡፡ ንቅናቄውን ምክንያት በማድረግም የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል እና የድሬዳዋ አሥተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ፋብሪካዎቹን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል፡፡ ፋብሪካዎቹም የከባድ መኪና ተሳቢ ማምረቻ፣ የባለ ሦስትና አራት እግር የመኪና መገጣጠሚያ፣ …