በአፋር ክልል ከቴምር ምርት የሚገኘውን ጥቅም ለማሳደግ እየተሠራ ነው
የቴምር ምርታማነትን በማስፋፋት ከዘርፉ የሚገኘውን ጥቅም ለማሳደግ በትኩረት እየተሠራ መሆኑን የአፋር ክልል እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ አስታወቀ። የክልሉ መልከዓ-ምድር እና የዓየር ጸባይ ለቴምር ተክል ምቹ ቢሆንም በሚፈለገው ልክ ከዘርፉ ተጠቃሚ መሆን አለመቻሉን በቢሮው የእርሻና ሆርቲካልቸር ልማት ዘርፍ የሆርቲካልቸር ልማት ዳይሬክተር አሕመድ አሚን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት በአፋምቦ እና አሳኢታ ወረዳዎች 302 ነጥብ 5 ሔክታር በቴምር …