የኢትዮ-ሳዑዲ ንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም መካሄድ ጀመረ
የኢትዮ-ሳዑዲ ንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም በአዲስ አበባ መካሄድ ጀምሯል። በፎረሙ ላይም የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ/ር)፣ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር)፣ የቱሪዝም ሚኒስትር አምባሳደር ናሲሴ ጫሊ፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል። ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) በፎረሙ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ በኢትዮጵያና ሳዑዲ ዓረቢያ መካከል ታሪካዊ የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት መኖሩን አስገንዝበዋል። …