Uncategorized

የኢትዮጵያ ሠነደ ሙዓለ-ንዋዮች ገበያ እና የካዛብላንካ አክሲዮን ገበያ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ

የኢትዮጵያ ሠነደ ሙዓለ-ንዋዮች ገበያ እና የካዛብላንካ አክሲዮን ገበያ (ካዛብላንካ ስቶክ ኤክስቼንጅ) ስትራቴጂካዊ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ። በስምምነቱ መሰረት የካዛብላንካ አክሲዮን ገበያ የኢትዮጵያ ሠነደ ሙዓለ-ንዋዮች ገበያን የቴክኒክ እና የሥራ አቅም የሚያሳድጉ ድጋፎችን ያደርጋል። ተቋሙ ደኅንነቱን የጠበቀ እና ቀልጣፋ የንግድ ሥርዓት እንዲፈጥር የቴክኖሎጂ ማዕቀፉን፣ የአሠራር አቅም እና የአደጋ አሥተዳደር አቅሙን የሚያጎለብቱ ሥራዎች እንደሚያከናውን ተገልጿል። ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት ምርቶችን …

የኢትዮጵያ ሠነደ ሙዓለ-ንዋዮች ገበያ እና የካዛብላንካ አክሲዮን ገበያ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ Read More »

የኢትዮጵያ ቡና በቻይና ገበያ ተፈላጊነቱ መጨመሩ ተነገረ

በጣዕሙ ለየት ያለው የኢትዮጵያ ቡና በቻይና ገበያ ተፈላጊነቱ እየጨመረ መምጣቱን በቤጂንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምክትል ሚስዮን መሪ አምባሳደር ደዋኖ ከድር ተናገሩ። አምባሳደር ደዋኖ በቻይና ንግድ ሚኒስቴር የቻይና ቡና ኢንዱስትሪ ማህበር እና ፕሮሞሽን ዳይሬክተር ዋንግ ቢን ከተመራ የተለያዩ የቡና ኩባንያ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱም የኢትዮጵያ የቡና ምርቶች አዳዲስ ገበያ ለማፈላለግ እንዲሁም በቻይና የቡና ኩባንያዎች ዘንድ ምርቱን ይበልጥ …

የኢትዮጵያ ቡና በቻይና ገበያ ተፈላጊነቱ መጨመሩ ተነገረ Read More »

የኢትዮጵያ ሠነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በመጪው ጥር ወር በይፋ ስራ ይጀምራል

የኢትዮጵያ ሠነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ ከመጪው ጥር ወር 2017 ጀምሮ በይፋ ስራ እንደሚጀምር የተቋሙ ዋና ስራ አስፈፃሚ ጥላሁን ኢስማኤል (ዶ/ር) ተናገሩ። ገበያው በኢትዮጵያ እያደገ ለመጣው የምጣኔ ኃብትና የፋይናንስ ፍላጎት አማራጭ እንደሚሆንም ተገልጿል። ተቋሙ ባለፈው አንድ ዓመት ኩባንያውን ዕውን ለማድረግ የተለያዩ ተግባራትን ሲያከናውን መቆየቱን ዋና ስራ አስፈጻሚው ገልፀዋል። በአሁኑ ወቅትም ተቋሙ ስራ ለመጀመር የሚያስችለውን ካፒታል የማሰባሰብ፤ …

የኢትዮጵያ ሠነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በመጪው ጥር ወር በይፋ ስራ ይጀምራል Read More »

የቻይናው ቢዋይዲ ኩባንያ ፎርድ እና ሆንዳን በመብለጥ የዓለማችን ቁጥር አንድ መኪና ሻጭ ተባለ

ኩባንያው በ2024 አራት ሚሊዮን መኪኖችን ሸጧል ቢዋይዲ በ2025 ስድስት ሚሊዮን መኪኖችን የመሸጥ እቅድ እንዳለውም አስታውቋል የቻይናው ቢዋይዲ ኩባንያ ፎርድ እና ሆንዳን በመብለጥ የዓለማችን ቁጥር አንድ መኪና ሻጭ ተባለ። በቻይናዋ ሸንዘን ማዕከሉን ታደረገው ቢዋይዲ የመኪና አምራች ኩባንያ አሁን ላይ በመኪና ሽያጭ የዓለማችን ቁጥር አንድ መሆን ችሏል። ኩባንያው የ2024 ዓመት ውስጥ ባሉት 11 ወራት ውስጥ 3 ነጥብ …

የቻይናው ቢዋይዲ ኩባንያ ፎርድ እና ሆንዳን በመብለጥ የዓለማችን ቁጥር አንድ መኪና ሻጭ ተባለ Read More »

የህዳር 25 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን ምን ይመስላል?

የግል ንግድ ባንኮች ለአንድ ዶላር ከ124 ብር ጀምሮ ተቀራራቢ የመግዣ ዋጋ አቅርበዋል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዶላርን በ122 ብር እየገዛ በ125 ብር እየሸጠ ነው ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ህዳር 25 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ ሀገር ገንዘቦችን …

የህዳር 25 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን ምን ይመስላል? Read More »

የኢትዮጵያ ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር መጭበርበራቸው ተገለጸ

በአጭበርባሪዎች ተመዝብረዋል የተባሉት 28 የኢትዮጵያ ባንኮች ናቸው የተመዘበረው ገንዘብ ከአምናው ጋር ሲነጻጸር በ300 ሚሊዮን ብር ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል የኢትዮጵያ ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር መጭበርበራቸው ተገለጸ። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዓመታዊ የገንዘብ ደህንነት ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል፡፡ የባንኩ ሪፖርት እስከ ሰኔ 2024 ድረስ ያሉ የገንዘብ እንቅስቀሴዎች ዙሪያ ትኩረቱን አድርጓል። ባንኩ በሪፖርቱ ላይ እንደጠቀሰው 28 የኢትዮጵያ ባንኮች …

የኢትዮጵያ ባንኮች 1 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር መጭበርበራቸው ተገለጸ Read More »

የኢትዮጵያ፣ ጅቡቲና ሱዳን የቴሌኮም ግሩፖች በጋራ ለመስራት ተስማሙ

በኢትዮ ቴሌኮም፣ ጅቡቲ ቴሌኮም እና ሱዳቴል መካከል የሆራይዘን ፋይበር ኢኒሼቲቭ ስትራቴጂያዊ አጋርነት በዛሬው እለት ይፋ ተደርጓል። የሀገራቱ የቴሌኮም ግሩፖች አፍሪካን ከተቀረው ዓለም ጋር ከፍተኛ አቅም ባለው የፋይበር ኮኔክቲቪቲ ለማስተሳሰር የሚያስችል “የሆራይዘን ፋይበር ኢኒሼቲቭ” የአጋርነት ስምምነት በዛሬው እለት ተፈራርመዋል። በተጨማሪም ስትራቴጂያዊ አጋርነቱ የቀጠናውን የዲጂታል መሠረተ ልማት ስብጥር የሚቀይር እጅግ አስተማማኝ እና የላቀ ኮኔክቲቪቲ መፍጠር የሚያስችል ከፍተኛ …

የኢትዮጵያ፣ ጅቡቲና ሱዳን የቴሌኮም ግሩፖች በጋራ ለመስራት ተስማሙ Read More »

በህዳር 24 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን የዶላር ዋጋ ስንት ደረሰ?

የግል ንግድ ባንኮች አንድ ዶላርን እስከ 124 ብር ገዝተው እስከ 127 ብር እየሸጡ ይገኛሉ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አንድ ዶላርን በ122 ብር እየገዛ በ125 ብር እየሸጠ ነው ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች በየእለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን ይፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ህዳር 24 ቀን 2017 ዓ.ም የውጭ …

በህዳር 24 የባንኮች የውጭ ምንዛሬ ተመን የዶላር ዋጋ ስንት ደረሰ? Read More »

ኢትዮጵያ አምስተኛው የጀርመን-አፍሪካ የንግድ ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው

ኢትዮጵያ በኬንያ ናይሮቢ እየተካሄደ በሚገኘው አምስተኛው የጀርመን-አፍሪካ የንግድ ጉባዔ ላይ ተሳትፎ በማድረግ ላይ ትገኛለች። በጉባዔው ላይ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ ኢትዮጵያን ወክለው እየተሳተፉ ይገኛሉ። የኬንያ የውጭ እና ዳያስፖራ ጉዳዮች ሚኒስትር ሙሳሊያ ሙዳቫዲ(ዶ/ር)፣ የጀርመን ምክትል መራሔ መንግስት ሮበርት ሀቤክ(ዶ/ር)፣ የአፍሪካ ሀገራት ልዑካን እና የግሉ ዘርፍ ተዋናዮች በጉባዔው ላይ ታድመዋል። የጀርመን የልማት ትብብር ተቋም(GIZ) ያዘጋጀው ይህ …

ኢትዮጵያ አምስተኛው የጀርመን-አፍሪካ የንግድ ጉባዔ ላይ እየተሳተፈች ነው Read More »

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከሚያስተዳድራቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ 10ሩ ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን አደጉ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከሚያስተዳድራቸው 13 ኢንዱስትሪ ፓርኮች መካከል 10ሩ ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ማደጋቸውን ኮርፖሬሽኑ አስታውቋል። ኢንዱስትሪ ፓርኮቹና የድሬዳዋ ነፃ የንግድ ቀጠና መካከል 10ሩ ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን ማደጋቸውን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ለኮርፖሬሽኑ ማሳወቁንም አመላክቷል። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ቦርድ ፓርኮቹ ያሉበትን ደረጃ በመገምገም ወደ ልዩ ኢኮኖሚ ዞንነት ለማደግ 10ሩ አስፈላጊውን መስፈርት በማሟላታቸው ወደ ልዩ ኢኮኖሚ …

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከሚያስተዳድራቸው ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ 10ሩ ወደ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን አደጉ Read More »