ዶላር በባንኮች በኩል እስከ 115 ብር እየተሸጠ ነው::
አሁን ባንኮች እያቀረቡበት ያለው ዋጋ ከጥቁር ገበያውም የበለጠ ሆኗል:: በሀገር ውስጥ ያለው ከፍተኛ የሆነ የውጭ ምንዛሪ እጥረት በኢትዮጵያ ያሉ ባንኮች በተለይም የግሎቹ ምንዛሪን ለሚጠይቋቸው ደንበኞች የሚያስከፍሉት ኮሚሽን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ለምንዛሪው እለታዊ መሸጫ ካወጣው የዋጋ ተመን በላይ መሆኑን ዋዜማ ካደረገችው ቅኝት መረዳት ችላለች። ለአንድ የአሜሪካ ዶላር ከግል ባንኮች እየተጠየቀ ያለው ኮሚሽንም ከ55 ብር እስከ 60 …