Uncategorized
ኮሚቴው የቻይና ባለሃብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲያመርቱ ጥረት እንደሚያደርግ ገለጸ
ቻይናውያን ባለሃብቶቹ በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ገብተው ማምረት እንዲችሉ እንደሚሠራ የኢትዮ ቻይና ወዳጅነት ኮርፖሬሽን ኮሚቴ አስታወቀ። የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ከኢትዮ ቻይና ወዳጅነት ኮርፖሬሽን ኮሚቴ ፕሬዚዳንት ቤቲ ዡ ጋር ተወያይተዋል። በውይይታቸውም፣ በኢትዮ ቻይና ወዳጅነት ኮርፖሬሽን ስር የሚገኙ አምራች ባለሃብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ገብተው እንዲያመርቱ ሊከናወኑ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ መክረዋል። በኢንዱስትሪ …
ኮሚቴው የቻይና ባለሃብቶች በኢንዱስትሪ ፓርኮች እንዲያመርቱ ጥረት እንደሚያደርግ ገለጸ Read More »
የኢትዮ-ሞሮኮ የቢዝነስ ፎረምን በጋራ ለማዘጋጀት ስምምነት ተደረገ
በመጪው 2024 የኢትዮጵያና ሞሮኮ የቢዝነስ ፎረምን በጋራ ለማዘጋጀት የሚያስችል ስምምነት ተደርጓል። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ በኢትዮጵያ የሞሮኮ አምባሳደር ከሆኑት ናሻ አልዊ ጋር ተወያይተዋል። በውይይታቸው በኢትዮጵያ የሞሮኮ ባለሀብቶች ሊሳተፉባቸው የሚችሉ የተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፍ አማራጮችን ማሳደግ በሚቻልበት ጉዳይ ዙሪያ ምክክር አድርገዋል። በተጨማሪም በመጪው 2024 የኢትዮጵያ ሞሮኮ የቢዝነስ ፎረምን በጋራ ለማዘጋጀት ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ከኮሚሽሙ ያገኘነው …
ወደ ጂቡቲ የሚደርገው በረራ በሣምንት 17 ጊዜ ሊሆን ነው::
አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2016 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሚቀጥለው ወር ጀምሮ ወደ ጂቡቲ የሚያደርገውን በረራ በሣምንት ወደ 17 ጊዜ አሳደገ፡፡ አየር መንገዱ ከፈረንጆቹ ኅዳር 1ቀን 2023 ጀምሮ ወደ ጂቡቲ የሚያደርገውን በረራ የሚያሳድገው ሦስት የሌሊት በረራዎችን በመጀመር መሆኑንም ጠቁሟል፡፡
የኖርዌይ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ማድረግ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ::
የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ለሊሴ ነሜ ከኢትዮጵያ የኖርዌይ አምባሳደር ስቲያን ክሪስቴንስን ጋር ተወያይተዋል። በውይይታቸውም፣ የኖርዌይ ባለሃብቶች የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት ዕድል እና አማራጮች በጥልቀት እንዲቃኙ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል። በተጨማሪም ባለሃብቶቹ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ዘርፎች እንዲሳተፉ በጋራ መስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መወያየታቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል። በኢትዮጰያ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ተሰማርተው ለሚገኙ ባለሃብቶች የጋራ የድጋፍ እና ክትትል ስራ ለመስራት የሚያስችል ምክክር …
የኖርዌይ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ማድረግ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ:: Read More »