የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮምሽን ከፓኪስታን ባለሃብቶች ጋር የኢንደስትሪ ፓርክ ልማት ፣ የፋርማሱቲካል እና የማሸጊያ ምርቶች አምራች ኢንደስትሪ ዘርፍ ላይ እንዲሳተፉ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡
የመግባቢያ ሰነዱን በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮምሽን ምክትል ኮምሽነር ዳንኤል ተሬሳ እና በፓኪስታን የባለሀብቶች ተወካይ የተፈረመ ሲሆን በኢትዮጵያ ለቀናት ቆይታ አድርጎ በሀገራችን እንዲሁም በአፍሪካ ገበያ ተሳታፊነቱን ለመጨመር እና ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት ካሳየው የፓኪስታን የኢንቨስትመንት እና ንግድ ልዑክ ቡድን ጉብኝት አካል ነው፡፡ በፋርማሱቲካል ዘርፉ እና በማሸጊያ ምርቶች አምራች ኢንደስትሪ በቦሌ ለሚ እና ቂሊንጦ ኢንደስትሪያል ፓርኮች ለመግባት እና ለማልማት …