Uncategorized

አፕል አይፎን 15ን ይፋ አደረገ!

አፕል የቀጣዩን ትውልድ አይፎን 15ን ዛሬ አስተዋውቋል። አዲስ ይፋ የተደረጉት ሞዴሎች ከዚህ ቀደሙ በተለየ የዩኤስቢ ሲ(USB Type-C) የቻርጀር መሰኪያ የሚኖራቸው እንደሆነ ተገልጿል። የአውሮፓ ህብረት አምና ባወጣው ህግ በአባለ ሃገራቱ የሚመረቱ ሁሉም ስልኮች ተመሳሳይ የዩኤስቢ ፖርት እንዲኖራቸው መባሉ ይታወሳል።

ቻይና የመንግሥት ሠራተኞቿ ከውጭ የሚገቡ ዲጂታል ቁሶችን እንዳይጠቀሙ አገደች

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1፣ 2015 ቻይና የመንግሥት ሠራተኞቿ ከውጭ የሚገቡ ዲጂታል ቁሶችን እንዳይጠቀሙ ማገዷን አስታወቀች፡፡ ቻይና ገደቡን የጣለችው ለሳይበር ደኅንነቴ ስጋት ነው በሚል ምክንያት መሆኑን ቲአርቲ ወርልድ ዘግቧል፡፡ በመሆኑም የቻይና የመንግሥት ሠራተኞች እና ሃላፊዎች አይ ፎንን ጨምሮ ማናቸውንም ከውጭ የሚገቡ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ቁሶችን እንዳይጠቀሙ አስጠንቅቃለች፡፡ ምንጭ፦ ዘ ዎል ስትሪት ጆርናል

የእስያ ሀገራት ግንኙነታቸውን አጠናክረው ከቀጠሉ በዓለም የሚፈጠሩ ለውጦችን በቀላሉ መቋቋም ይችላሉ  – ሊ ችያንግ

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1/ 2015 የእስያ ሀገራት ያላቸውን ግንኙነት አጠናክረው የሚቀጥሉ ከሆነ በዓለም የሚፈጠሩ አዳዲስ ለውጦችን በቀላሉ መቋቋም እንደሚችሉ የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ችያንግ ተናገሩ፡፡ 26ኛው የቻይና -ኤስያ የመሪዎች ጉባኤ በኢንዶኖዥያ ጃካርታ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ በጉባኤው የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊ ችያንግ፣ የቻይናና የሌሎች የእስያ ሀገራት ትብብር በብዙ አስቸጋሪ ጊዜያት ሳያናወጥ ለረጅም ጊዜ መቆየት መቻሉን አንስተዋል፡፡ ቻይናን …

የእስያ ሀገራት ግንኙነታቸውን አጠናክረው ከቀጠሉ በዓለም የሚፈጠሩ ለውጦችን በቀላሉ መቋቋም ይችላሉ  – ሊ ችያንግ Read More »

ቻይና ግማሽ ቢሊየን ዶላር የኢትዮጵያን ዕዳ መክፈያ ጊዜ አራዘመች

Photo credit- PM office የኢትዮጵያ ዋነኛ አበዳሪ፣ ቻይና ፣ በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር እስከ 2024 ድረስ መክፈል የሚጠበቅባትን ግማሽ ቢሊየን ዶላር የኢትዮጵያን ዕዳ መክፈያ ጊዜ አራዘመች። ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ኢትዮጵያ አባልነቷ ተቀባይነት ባገኘበት የደቡብ አፍሪካው የጆሀንስበርግ የብሪክስ ጉባኤ ላይ ከቻይናው ፕሬዝዳንት ቪ ጂንፒንግ ጋር በነበራቸው ውይይት ነበር የብድር እፎይታው ይፋ የተደረገው። ሆኖም በወቅቱ ስለ ብድር እፎይታው …

ቻይና ግማሽ ቢሊየን ዶላር የኢትዮጵያን ዕዳ መክፈያ ጊዜ አራዘመች Read More »