Uncategorized

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለኢንቨስትመንት ተመራጭ መሆናቸውን የጃፓን ባለሀብቶች ገለፁ

 የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለኢንቨስትመንት ተመራጭ መሆናቸውን በኢትዮ-ጃፓን የኢንቨስትመንት ፎረም የተሳተፉ የጃፓን ባለሀብቶች ገለፁ። በፎረሙ የተሳተፉ የጃፓን ባለሀብቶች እና የተለያዩ የሥራ ኃላፊዎች በኢትዮጵያ የቦሌ ለሚና ቂሊንጦ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን ጎብኝተዋል። የልዑካን ቡድኑ አባላት በጉብኝታቸው የፓርኮቹን መሰረተ ልማት፣ ወቅታዊ የስራ እንቅስቃሴ እንዲሁም የባለሀብቶችን ተሳትፎ ተመልክተዋል። በፓርኮቹ መዋዕለ ንዋያቸውን ቢያፈሱ ስለሚያገኟቸው የኢንቨስትመንት አስቻይ ሁኔታዎችና ማበረታቻዎች ዙሪያም ገለፃ ተደርጎላቸዋል። በኮርፖሬሽኑ …

የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ለኢንቨስትመንት ተመራጭ መሆናቸውን የጃፓን ባለሀብቶች ገለፁ Read More »

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ስፔን ማድሪድ ከተማ በድጋሚ በረራ ጀመረ 

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለሦስት ዓመታት ተኩል አቋርጦት የነበረውን ወደ ስፔን ማድሪድ ከተማ በረራ በድጋሚ ጀመረ። አየር መንገዱ በሳምንት 4 ጊዜ ወደ ስፔን ማድሪድ በረራ የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል። አየር መንገዱ በረራ መጀመሩን አስመልክቶ ባዘጋጀው የማብሰሪያ መርኃ ግብር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው፣ በኢትዮጵያ የስፔን አምባሳደር …

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ስፔን ማድሪድ ከተማ በድጋሚ በረራ ጀመረ  Read More »

የታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

የታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል ተብሏል። የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከኅዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ባለበት እንደሚቀጥል የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል። ቀደም ሲል የነበረው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ስንት ነው ? ምንጭ፦ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር

አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከ3 ነጥብ 8 ሚሊየን ኩንታል በላይ የቡና ምርት መሰብሰቡን አስታወቁ

በ2016 የምርት ዘመን 11 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል የቡና ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱን እና እስካሁን ከ3 ነጥብ 8 ሚሊየን ኩንታል በላይ መሰብሰቡን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ አስታወቁ፡፡ አፈፃፀሙ በምርት መጠንና ፍጥነት የተቀመጡት ግቦች እየተሳኩ መሆናቸውን ያመለክታል ሲሉ ርዕሰ መስተዳድሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡ ከግብርናው ዘርፍ ዓላማዎች አንዱ የወጪንግድን ማሳደግ መሆኑን ጠቁመው ÷ ይህንን ግብ …

አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከ3 ነጥብ 8 ሚሊየን ኩንታል በላይ የቡና ምርት መሰብሰቡን አስታወቁ Read More »

በዱባይ የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት አቅም ለማስተዋወቅ ያለመ የቢዝነስ ፎረም ተካሄደ

በዱባይ እየተካሄደ ካለው 28ኛው ዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ጎን ለጎን የኢትዮጵያን እምቅ የኢንቨስትመንት አቅም ለማስተዋወቅ ያለመ የቢዝነስ ፎረም ተካሄዷል፡፡ በዚህ ፎረም ላይ በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የሚገኙና በኢትዮጵያ የመሰማራት አቅም ያላቸው ከ30 በላይ ኩባንያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ እያስመዘገበች ስላለው ስኬት፣ በዘርፉ የግል ባለሀብቶች ሚና …

በዱባይ የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት አቅም ለማስተዋወቅ ያለመ የቢዝነስ ፎረም ተካሄደ Read More »

የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ወደ ካዛብላንካ የጭነት ማጓጓዝ በረራ ሊጀምር ነው

የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ወደ ሞሮኮ – ካዛብላንካ አዲስ የጭነት ማጓጓዝ በረራ ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል። ወደ ካዛብላንካ የሚያርገው የጭነት በረራ በሰሜን አፍሪካ የመጀመሪያው መሆኑን የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። ወደ ካዛብላንካ የሚደረገውን የጭነት በረራ ጨምሮም ዓየር መንገዱ በአፍሪካ የሚያደርጋቸው የጭነት በረራዎች ቁጥር ወደ 34 ከፍ ማለቱ ተገልጿል። ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ