ክልሉ ለኢንቨስትመንት የሚውል 58 ሺህ ሄክታር መሬት አዘጋጅቷል
በ2016 በጀት ዓመት ለኢንቨስትመንት የሚሆን 58 ሺህ ሄክታር መሬት ማዘጋጀቱን የኦሮሚያ ክልል ኢንቨስትመንትና ኢንዱስትሪ ቢሮ አስታወቀ። በዘርፉ ለ500 ሺህ ዜጎች የሥራ ዕድል ለመፍጠር ታቅዷል። የቢሮው ኃላፊ አሕመድ እንድሪስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ በ2016 በጀት ዓመት በክልሉ የሚገኙ የኢንቨስትመንት አማራጮችን ወደሥራ ለማስገባት እየተሠራ ነው። በተያዘው በጀት ዓመት ባለሀብቶች በተለያዩ ዘርፎች ተሰማርተው የሚያለሙበት 58 ሺህ ሄክታር መሬት …