የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት 1 ሺህ 585 ፍቃዶችን ሰጠ
የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤት በንግድ ምልክት፣ በፓተንት፣ የቅጅና ተዛማጅ መብቶችን ጨምሮ በአጠቃላይ 1 ሺህ 585 ፍቃዶችን ሰጠ። የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረት ጽ/ቤት የደንበኞች አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ ኤልያስ ጥሩነህ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጹት፥ ተቋሙ ፈቃዱን የሰጠው በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያ አራት ወራት ውስጥ ነው። በዚህም ንግድ ምልክት፣ ፓተንት ፍቃድና ኢንዱስትሪያል ዲዛይንን ጨምሮ በተለያዩ ዘርፎች ፍቃድ መሰጠቱን …







