በኢትዮጵያ የቢትኮይን ማይኒንግ የመረጃ ማዕከል ሊገነባ መሆኑ ተገለፀ።
የሩሲያው የቢትኮይን ማይኒንግ አቅራቢ ድርጅት “ቢትክሉስተር” በኢትዮጵያ 120 ሜጋ ዋት የቢትኮይን የመረጃ ማዕከል ለማቋቋም ማቀዱን ይፋ አድርጓል (https://bitcluster.ru/mass-media/from-the-arctic-to-africa.html)። ቢትኮይን ማይኒንግ ምንድነው? የቢትኮይን ማይኒንግ በቢትኮይን የሚፈፀሙ ግብይቶች አስተማማኝ እና እምነት የሚጣልባቸው መሆናቸውን ለማረጋገጥ የሚረዳ ስርዓት ነው። የመረጃ ማዕከሉ የሚገነባው በአዲስ አበባ ከፍተኛ-ቮልቴጅ ማከፋፈያ ጣቢያ ባለበት ቂሊንጦ አካባቢ ሲሆን 30,000 ካሬ ሜትር ላይ የሚያርፍ ነው ተብሏል። አዲሱ …