ቻይና በዓለም አቀፍ የመርከብ ግንባታ ዘርፍ ቀዳሚነቷን አረጋገጠች
ቻይና በዓለም አቀፍ የመርከብ ግንባታ ዘርፍ ለ14 ተከታታይ ዓመታት በቀዳሚነት መቀጠሏ ተገለጸ። ቻይና ባለፈው ዓመት ውስጥ በምርታማነት፣ በአዳዲስ ትዕዛዞች እና ቀደም ብለው በተሰጡ ትዕዛዞች ጠንካራ እድገት እያሳየች መምጣቷን አስመስክራለች ተብሏል። በእነዚህ ሦስት ዋና ዋና አመላካቾችም በዓለም አቀፍ የመርከብ ግንባታ ገበያ ውስጥ ለ14 ተከታታይ ዓመታት የመሪነቱን ሥፍራ መያዟን የኢንዱስትሪ እና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያወጣው መረጃ ያሳያል። …