Uncategorized

አምባሳደር ምስጋኑ ከኢንዶኔዢያ አምባሳደር፣ ከየመን ኤምባሲ ጉዳይ ፈጻሚ እና ከኒውዚላንድ አምባሳደር ጋር መከሩ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ የኢንዶኔዢያ አምባሳደር ቡሲራ ባንሱር፣ ከየመን ኤምባሲ ጉዳይ ፈጻሚ አምባሳደር ያህያ አል ኤሪያኒ እና ከኒውዚላንድ አምባሳደር ሚካኤል አፕቶን ጋር ተወያይተዋል፡፡ ውይይታቸውም በሁለትዮሽ እና በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ያተኮረ እንደሆነም ነው የተገለጸው፡፡ አምባሳደር አል ቡሲራ ባንሱር፥ ኢትዮጵያና ኢንዶኔዢያ ያላቸውን ግንኙነት በማድነቅ፥ በሁለቱ ሀገራት መካከል በተለይም በንግድ፣ ኢኮኖሚ እና ኢንቨስትመንት ላይ …

አምባሳደር ምስጋኑ ከኢንዶኔዢያ አምባሳደር፣ ከየመን ኤምባሲ ጉዳይ ፈጻሚ እና ከኒውዚላንድ አምባሳደር ጋር መከሩ Read More »

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት ይቀጥላል

የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በጥር ወር ሲሸጥ በነበረበት ዋጋ የሚቀጥል መሆኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል። በዚህም መሰረት ከጥር 28 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በሥራ ላይ በነበረበት ዋጋ እንዲቀጥል መወሰኑ ተገልጿል።

ከቪዛ ነፃ የሆነ ጠንካራ ሁለተኛ ፓስፖርት ልናገኝ የምንችልባቸው 10 ሀገራት የትኞቹ ናቸው?

በሀገራቱ ፓስፖርቶች ያለ ቪዛ ከ103 እስከ 192 ሀገራት መጓዝ ያስችላሉ አፍሪካዊ ከመሆን ጋር ተያይዞ ከሚያጋጥሙን ችገሮች ውስጥ አንዱ የአፍሪካ ፓስፖርት ይዘን በምንንቀሳቀስበት ጊዜ የሚያጋጥመን የጉዞ ገደብ ነው። በርካታ አፍሪካውያን ቪዛ መከልከል፣ ጥብቅ የጉምሩክ ሥርዓት ማለፍን ጨምሮ፣ አልፎ ተርፎም በአፍሪካ ፓስፖርታቸው ምክንያት እስከ መታሰርም ደርሰዋል። ለዚህም መፍትሄ ሊሆን የሚችል አማራጭ ሁለተኛ ፓስፖርት መያዝ ሲሆን፤ ለዚህም ደግሞ …

ከቪዛ ነፃ የሆነ ጠንካራ ሁለተኛ ፓስፖርት ልናገኝ የምንችልባቸው 10 ሀገራት የትኞቹ ናቸው? Read More »

የጉምሩክ ኮሚሽን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪካል ካርጎ ትራኪንግ ቴክኖሎጂ አተገባበር ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አካሄደ።

የጉምሩክ ኮሚሽነር ደበሌ ቃበታ ካሁን ቀደም ይህንን ቴክኖሎጂ ተግባራዊ ለማድረግ ጥረቶች ቢደረጉም በአንዳንድ ችግሮች ምክንያት ተግባራዊ ሳይደረግ መቆየቱን ገልጸዋል። መንግሥት ለጉዳዩ ልዩ ትኩረት በመስጠቱ ቴክኖሎጂውን ተግባራዊ ማድረግ የሚያስችል ደረጃ ላይ መደረሱን የተናገሩት ኮሚሽነሩ ቴክኖሎጂው ተግባራዊ እንዲደረግ ጥረት ላደረጉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የትራንስፖርትና ሎጂስቲክ ሚንስትሩ ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በበኩላቸው ይህ ቴክኖሎጂ በዓለም ላይ ተግባራዊ መደረግ ከጀመረ …

የጉምሩክ ኮሚሽን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪካል ካርጎ ትራኪንግ ቴክኖሎጂ አተገባበር ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር አካሄደ። Read More »

ከማዕድን ወጪ ንግድ 142 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ ተገኘ።

ባለፉት 6 ወራት ከማዕድን ወጪ ንግድ 142 ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የማዕድን ሚኒስቴር አስታውቋል። ገቢው ለውጪ ገበያ ከቀረቡ የወርቅ፣ ታንታለም፣ ሊቲየም ኦር፣ ጌጣጌጥና የኢንዱስትሪ ማዕድናት የተገኘ መሆኑ ተገልጿል። ሕገ-ወጥ የማዕድን ምርትና ግብይትን ለመቅረፍ የተጠናከረ ክትትልና ቁጥጥር ሥራ እንደሚከናወን መጠቆሙንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል።

በተለያዩ ሀገራት የኢትዮጵያ አምባደሮች ኢንቨስትመንቶችን እየጎበኙ ነው

በተለያዩ ሀገራት የኢትዮጵያ አምባደሮች በግል አልሚዎች እየለሙ የሚገኙ ኢንቨስትመንቶችን እየጎበኙ ነው። አምባደሮች በፌዳ ዋቅ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ጎልድ የኢንዱስትሪ መንደርን ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ አምባሳደር ስለሺ በቀለ (ዶ/ር)፣ አምባሳደር ባጫ ደበሌ፣ አምባሳደር ሌንጮ ባንቲ፣ አምባሳደር ብርሃኑ ፀጋዬን ጨምሮ ሌሎች ዲፕሎማቶችም ተሳትፈዋል። የጉብኝታቸው አላማም የቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፍሰትን ለተቀረው ዓለም ማስተዋወቅ፣ የሀገር ውስጥ አልሚዎችን ከተወከሉባቸው ሀገራት ባለሀብቶች ጋር …

በተለያዩ ሀገራት የኢትዮጵያ አምባደሮች ኢንቨስትመንቶችን እየጎበኙ ነው Read More »

በመዲናዋ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ለማከናወን ከሲጂሲኦሲ የግንባታ ተቋራጭ ጋር ስምምነት ተፈረመ

ከዓለም ባንክ በተገኘ የ145 ሚሊየን ዶላር በአዲስ አበባ ከተማ የምስራቅ ተፋሰስ ፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ለማከናወን ከሲጂሲኦሲ የግንባታ ተቋራጭ ጋር ስምምነት ተፈረመ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ፕሮጀክቱ ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ የከተማዋን ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አመልክተዋል። በሶስት ዓመት ጊዜ ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የሚጠበቀው ፕሮጀክቱ በዋነኛነት ከዚህ ቀደም …

በመዲናዋ የፍሳሽ ማጣሪያ ጣቢያ ግንባታ ለማከናወን ከሲጂሲኦሲ የግንባታ ተቋራጭ ጋር ስምምነት ተፈረመ Read More »

የምርት ጥራት ደረጃ አላሟሉም በተባሉ 92 ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ

የምርት ጥራት ደረጃ ባላሟሉ 92 ድርጅቶች ላይ የእርምት እርምጃ ወስጃለሁ አለ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር በ282 ድርጅቶች ላይ የምርት ጥራት ቁጥጥር ሥራ ተከናውኖ 60ዎቹ የጥራት ደረጃ ማሟላታቸው ተገልጿል። እንዲሁም 130 ድርጅቶች  ማስተካከያ አድርገው የተቀመጠውን መስፈርት እንዲያሟሉ መደረጉም ተጠቅሷል። 92 ድርጅቶች ደግሞ የተቀመጠውን የጥራት ደረጃ ያላሟሉና ከደረጃ በታች በመሆናቸው እርምጃ መወሰዱን የሚኒስቴሩ መረጃ አመላክቷል። ማኅበረሰቡም የሚሸምተውን …

የምርት ጥራት ደረጃ አላሟሉም በተባሉ 92 ድርጅቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ Read More »

የቻይና ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ ኬሚካልና የብረታብረት ማምረቻ ዘርፎች ያላቸውን ተሳትፎ እንዲያጠናክሩ ጥሪ ቀረበ

የቻይና ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ ኬሚካልና የብረታብረት ማምረቻ ዘርፎች ያላቸውን ተሳትፎች እንዲያጠናክሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ ጥሪ አቀረቡ። ሚኒስትር ዴኤታው በቻይና የዓለም አቀፍ ንግድ ግንኙነቶች ማስተዋወቂያ ካውንስል ምክትል ሊቀመንበር ዣንግ ዣኦግንግ ከተመራው የቻይና የንግድ ልኡክ ጋር ተወያይተዋል። ሚኒስትር ዴኤታው ለልዑኩ በኢትዮጵያ ስላለው የኢንቨስትመንትና የንግድ እድሎች ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን የቻይና ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በተለይ …

የቻይና ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በአግሮ ፕሮሰሲንግ፣ ኬሚካልና የብረታብረት ማምረቻ ዘርፎች ያላቸውን ተሳትፎ እንዲያጠናክሩ ጥሪ ቀረበ Read More »

ቻይና ከ4 ሚሊየን በላይ የሀገር ውስጥ የፈጠራ ባለቤትነት በመያዝ የመጀመሪያዋ ሀገር ሆነች

ቻይና በፈረንጆቹ 2023 መጨረሻ ወደ ከ4 ሚሊየን በላይ የሀገር ውስጥ የፈጠራ ባለቤትነትን በመያዝ የመጀመሪያዋ ሀገር መሆን መቻሏ ተገልጿል። ይህም ከዓመት ዓመት በ22 ነጥብ 4 በመቶ እያደገ መምጣቱን ተከትሎ በዓለም የመጀመሪያዋ ሀገር እንዳደረጋት የሀገሪቱ ብሔራዊ አዕምሯዊ ንብረት አስተዳደር አስታውቋል። የአስተዳደሩ ምክትል ኃላፊ ሁ ዌንሁይ ከፍተኛ ዋጋ ያላቸው የፈጠራ ባለቤትነት ምዝገባዎች ከጠቅላላው ከ40 በመቶ በላይ መሆናቸውን አመላክተዋል። …

ቻይና ከ4 ሚሊየን በላይ የሀገር ውስጥ የፈጠራ ባለቤትነት በመያዝ የመጀመሪያዋ ሀገር ሆነች Read More »