በጂቡቲ ወደብ ላይ የቆይታ ጊዜያቸው ያለፈ ተሸከርካሪዎች በባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ተጓጉዘው ወደ አገር ከገቡ በኋላ ድሬዳዋ ደረቅ ወደብ እንዲቆዩ ተወሰነ።
ሚኒስቴሩ፦➡️ ለባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት➡️ ለጉምሩክ ኮሚሽን በጻፈው ደብዳቤ፣ የተሽከርካሪዎቹ አስመጪዎች በሚያቀርቡት መረጃ መሠረት፣ በየወቅቱ በጂቡቲ ወደብ የተከማቹ ተሽከርካሪዎችን መጠንና የቆይታ ጊዜ ከጂቡቲ ወደብ ባለሥልጣንና ከጉሙሩክ ኮሚሽን እንዲሰበሰብ አዟል። የባህር ትራንስፖርት የሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የወደብ ፎርማሊቲ አሟልቶ ተገቢ ክፍያ በመፈጸምና በድሬዳዋ ደረቅ ወደብ ማከማቻ ሥፍራ በማዘጋጀት ተለዋጭ ውሳኔ እስኪሰጥ በራሱ ኃላፊነት እና በራሱ ወጪ …