Uncategorized

የህንድ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀረበ

የህንድ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ እንዲሳተፉ በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ ጥሪ አቀረቡ። በህንድ ሙምባይ ከተማ የእስያ አፍሪካ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ያዘጋጀው ስድስተኛው ዓለም አቀፍ የንግድ አመራሮች ፎረም ተካሂዷል። አምባሳደሩ በፎረሙ ላይ እንደገለጹት÷ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የግብርና፣ የማምረቻ፣ የማዕድን፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና ቱሪዝም ዘርፎች ቅድሚያ የሚሰጣቸው የኢንቨስትመንት መስኮች ናቸው። በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት …

የህንድ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀረበ Read More »

የኢትዮጵያ ስታርት አፕ ዐውደ-ርዕይ ተከፈተ

 570 ስታርት አፖች የሚሳተፉበት የኢትዮጵያ ስታርት አፕ ዐውደ-ርዕይ በሣይንስ ሙዚየም ተከፈተ። ለሦስት ሣምንታት በሚቆየው ዐውደ-ርዕይ ላይ÷ የመጀመሪያ ደረጃ፣ የመጀመሪያ ደረጃን የተሻገሩ እና ወደገበያ የመቀላቀል ደረጃ ላይ የደረሱ ስታርት አፖች  ሥራዎቻቸውን አቅርበዋል። የሥራ እና ክኅሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃያት ካሚል፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) እና ሌሎች …

የኢትዮጵያ ስታርት አፕ ዐውደ-ርዕይ ተከፈተ Read More »

አየር መንገዱ ወደ አንጎላ ሉዋንዳ ከተማ ዕለታዊ በረራ ጀመረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አንጎላ ሉዋንዳ ከተማ የሚያደርገውን በረራ ዕለታዊ ማድረጉን አስታወቀ። ወደ አንጎላ ሉዋንዳ ከተማ ሲደረግ የነበረው ሳምንታዊ በረራ በየዕለቱ እንዲሆን መደረጉ መንገደኞች የተመቸ የጉዞ አማራጭ እንዲኖራቸው እንደሚያስችል አየር መንገዱ አስታውቋል።

የቻይናው ሲኢኢሲ ኩባንያ በኢትዮጵያ በተለያዩ ኢንቨስትመንቶች መሰማራት እፈልጋለሁ አለ

የቻይና ኢነርጂ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሲኢኢሲ) ኩባንያ በአዳዲስ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ እንዲሁም በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር መስራት እንደሚፈልግ ገለጸ። የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ከኩባንያውን ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል። የኩባንያው ኃላፊዎችም በውይይቱ ላይ አዳዲስ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመገንባት፣ የግንባታ ግብዓቶችን እና የኤሌክትሪካል ቁሶችን በማምረት እንዲሁም በሌሎች የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመሰማራት …

የቻይናው ሲኢኢሲ ኩባንያ በኢትዮጵያ በተለያዩ ኢንቨስትመንቶች መሰማራት እፈልጋለሁ አለ Read More »

ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይት በሁሉም ባንኮች እንደሚጀመር አስታወቀ

በውስን የክፍያ አማራጮች ብቻ የነበረው የነዳጅ ግብይት በቀጣይ በሁሉም ባንኮች እንደሚጀመር የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል። የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር በቀለች ኩማ እንዳሉት÷ ከነዳጅ ግብይትጋር በተያያዘ በተገልጋዮችና ሌሎች ባንኮች የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት አገልግሎቱን ማስፋት አስፈልጓል። በዚህ መሰረትም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ እና በቴሌ ብር ብቻ ሲደረግ የነበረው የነዳጅ ግብይት ዲጂታል የክፍያ አማራጮችን በማስፋት ሌሎች …

ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይት በሁሉም ባንኮች እንደሚጀመር አስታወቀ Read More »

ሁዋዌ የቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ኩባንያ የፋይናንስ ዘርፉን በዲጂታል ለማገዝ ያለመ መድረክ እያካሄደ ነው

 ሁዋዌ የቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ኩባንያ የፋይናንስ ዘርፉን በዲጂታል ለማገዝ ያለመ መድረክ እያካሄደ ይገኛል። ተቋሙ በኢትዮጵያ የዲጂታል ሳምንት መርሀ ግብር ካለፉት ቀናት ጀምሮ ሲያካሂድ ቆይቷል። የኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የ2025 ዕቅድን እውን ለማድረግ ብሎም የፋይናንስ ዘርፉን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የዲጂታል ሳምንቱ አስቻይ ሁኔታን የሚፈጥር እንደሆነ ተመላክቷል። መድረኩ የዲጂታል ፋይናንስ ስርዓቱ የዘመነ እንዲሆንና ደህንነቱ የተጠበቀ የፋይናንስ አገልግሎት እንዲኖር የሚያግዝ እንደሆነ …

ሁዋዌ የቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ኩባንያ የፋይናንስ ዘርፉን በዲጂታል ለማገዝ ያለመ መድረክ እያካሄደ ነው Read More »

ዝቅተኛ የብድር ጨና ያለባቸው ዓለማችን ሀገራት የትኞቹ ናቸው?

ኩዌት፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ እ ቦትስዋና ዝቅተኛ የብድር ጫና ካለባቸው ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው የሩቅ ምስራቋ ጃፓን ከዓመታዊ ትርፏ በላይ የሆነ የብድር ጫና ያለባት ቀዳሚዋ ሀገር ናት ዝቅተኛ የብድር ጨና ያለባቸው ዓለማችን ሀገራት የትኞቹ ናቸው? እንደ ዓለም አቀፉ የፋይናንስ ተቋም አይኤምኤፍ ሪፖርት ከሆነ ኩዌት ያለባት ብድር ከዓመታዊ ኢኮኖሚዋ ወይም ጂዲፒ 11 በመቶ ያህል ብቻ ነው አፍሪካዊቷ …

ዝቅተኛ የብድር ጨና ያለባቸው ዓለማችን ሀገራት የትኞቹ ናቸው? Read More »

ዌንዡ ኒክሲን ትሬዲንግ ኩባንያ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ወረቀት የማምረት ፍላጎት አለኝ አለ

300 ሚሊየን ዶላር ካፒታል ያለው የቻይናው ዌንዡ ኒክሲን ትሬዲንግ ኩባንያ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ወረቀት የማምረት ፍላጎት እንዳለው አስታውቋል። የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ከኩባንያው አመራሮች ጋር ባደረጉት ውይይት÷ የኩባንያው አመራሮች ስለ ኢንቨስትመንት ዕቅዳቸው ዝርዝር መረጃዎችን አቅርበዋል። አቶ አክሊሉም በኮርፖሬሽኑ የሚገኙ የኢንቨስትመንት ማዕከሎችን፣ ማበረታቻዎችን፣ የመሰረተ-ልማትና የአገልግሎት አሰጣጥን የተመለከቱ መረጃዎችን አስረድተው÷ ኮርፖሬሽኑ ለኩባንያው …

ዌንዡ ኒክሲን ትሬዲንግ ኩባንያ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ወረቀት የማምረት ፍላጎት አለኝ አለ Read More »

የሁቲ ታጣቂዎች በቀይ ባህር ላይ በሚሰነዝሩት ጥቃት ኤክስፖርተሮች መስተጓጎል እየገጠማቸው መሆኑ ተነገረ

የሁቲ ታጣቂዎች በቀይ ባህር የጭነት መርከቦች ላይ በሚፈጸሙት ጥቃት ሳቢያ፣ ትልልቅ የመርከብ ኩባንያዎች ወደ አካባቢው ስለማይመጡ፣ ኤክስፖርተሮች ከባድ ችግር ውስጥ መውደቃቸውንና በሥራቸው ላይም መስተጓጎል እየገጠማቸው እንደሆነ ተገለጸ። የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ባለፉት ዘጠኝ ወራት ውስጥ በ401 ባለሃያ ጫማ ኮንቴይነሮች 9,303.54 ሜትሪክ ቶን ወጪ ጭነት በራሱ መርከቦች ወደ ቻይና፣ ህንድና የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ማጓጓዙ …

የሁቲ ታጣቂዎች በቀይ ባህር ላይ በሚሰነዝሩት ጥቃት ኤክስፖርተሮች መስተጓጎል እየገጠማቸው መሆኑ ተነገረ Read More »

የሳይመንስ ኩባንያ በኢትዮጵያ የኢነርጂ ልማት አማራጮች ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳለው ገለፀ

 የሳይመንስ ኢነርጂ ኩባንያ በኢትዮጵያ ባሉት የኢነርጂ ልማት አማራጮች ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳለው ተገለፀ። የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ሀብታሙ ኢተፋ (ዶ/ር፣ ኢ/ር) በኢትዮጵያና በአፍሪካ ህብረት የጀርመን አምባሳደር ስቴፋን አወር እና ከሳይመንስ ኢነርጂ ኩባንያ ተወካይ ጋር ተወያይተዋል። ውይይቱ በኢነርጂ ልማት ኢንቨስትመንት ዙሪያ ያተኮረ ሲሆን በዚህ ወቅት ሀብታሙ ኢተፋ(ዶ/ር፣ ኢ/ር)÷ የሀይል አቅርቦት ብቃትና ውጤታማነት ላይ የሚያግዙ የግሉ ዘርፍ ኩባንያዎች …

የሳይመንስ ኩባንያ በኢትዮጵያ የኢነርጂ ልማት አማራጮች ላይ ለመሳተፍ ፍላጎት እንዳለው ገለፀ Read More »