Uncategorized

በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ 2025 የቢዝነስ ፎረም ግንቦት 4 እና 5 በአዲስ አበባ ይካሄዳል

በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ 2025 ከፍተኛ የቢዝነስ ፎረም በመጪው ግንቦት 4 እና 5 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ ተገለጸ። ፎረሙን በተመለከተ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) እና የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ሰመሪታ ሰዋሰው ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተዋል። የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዘለቀ ተመስገን (ዶ/ር) እንደተናገሩት፥ የቢዝነስ ፎረሙ በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ በገንዘብ ሚኒስቴር እና በአጋር …

በኢትዮጵያ ኢንቨስት ያድርጉ 2025 የቢዝነስ ፎረም ግንቦት 4 እና 5 በአዲስ አበባ ይካሄዳል Read More »

ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ቱሪዝምን ለማሳደግ የሚያግዛትን ስምምነት ፈረመች

ኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍን ለማሳደግ የሚያስችላትን ስምምነት በአፍሪካ ጉዞና ቱሪዝምን ለማስፋፋት ከሚሠራው አፍሪካ ትራቭል ኮኔክት ጋር ስምምነት ፈርማለች። ስምምነቱን የፈረመው በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በማኅበራዊ ትስስር ገፁ ባወጣው መረጃ፤ ስምምነቱ በርካታ ዕድሎችን የሚፈጥር ነው። ይህም የሀገሪቱን ልዩ እና ማራኪ መዳረሻዎች በማስተዋወቅ ተደራሽነትን እንደሚጨምር ገልጿል። በተጨማሪም ኢትዮጵያ ቅርሶቿንና መልክዓ-ምድሮቿን እንዲሁም ልዩ የቱሪዝም መዳረሻዎቿን በማስተዋወቅ፤ በአፍሪካ ቀዳሚ የጉዞ መዳረሻ …

ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ ቱሪዝምን ለማሳደግ የሚያግዛትን ስምምነት ፈረመች Read More »

የቱርክ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ማድረግ እንደሚፈልጉ ገለጹ

የቱርክ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ ዘርፎች መዋዕለ ንዋያቸውን ማፍሰስ እንደሚፈልጉ ገልጸዋል። በቱርክ የኢትዮጵያ አምባሳደር አደም መሃመድ በተለያዩ ዘርፎች ከተሰማሩ የቱርክ ኩባንያዎች ተወካዮችና ባለሃብቶች ጋር ተወያይተዋል። አምባሳደሩ በዚሁ ወቅት፥በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችን፣ የፋይናንስ ዘርፉንና የኢንቨስትመንት ማበረታቻዎችን በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል። ባለሃብቶቹ ለተደረገላቸው ገለጻ አመስግነው፥ በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች መሰማራት እንደሚፈልጉ መግለጻቸውን የኤምባሲው መረጃ ያመላክታል። ኩባንያዎች በቅርቡ በኢትዮጵያ በሚካሄዱት …

የቱርክ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት ማድረግ እንደሚፈልጉ ገለጹ Read More »

የአረብ ኤምሬትስ እና አሜሪካ ግዙፍ ኢኮኖሚያዊ ትስስር አመላካች አሃዞች

የሁለቱ ሀገራት የንግድ ልውውጥ ከ30 ቢሊየን ዶላር በላይ ደርሷል አረብ ኤምሬትስ ከአሜሪካ ጋር ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመረችው እንደ ሀገር በተመሰረተች (በፈረንጆቹ 1971) ማግስት ነው። በዋሽንግተን የሚገኘው የኤምሬትስ ኤምባሲ በይፋ የተመረቀው በ1974 ሲሆን፥ አሜሪካም በተመሳሳይ አመት በአቡዳቢ ኤምባሲዋን ከፍታለች። የ50 አመታት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው አረብ ኤምሬትስ እና አሜሪካ በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በንግድ እና ቴክኖሎጂ ዘርፎች ጠንካራ ትስስር …

የአረብ ኤምሬትስ እና አሜሪካ ግዙፍ ኢኮኖሚያዊ ትስስር አመላካች አሃዞች Read More »

ከወጪ ንግድ 4 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል- ካሣሁን ጎፌ (ዶ/ር)

ኢትዮጵያ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከወጪ ንግድ 4 ነጥብ 5 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ ማግኘቷን የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስትር ካሣሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ። የሚኒስቴሩ እና ተጠሪ ተቋማቱ አመራሮች የበጀት ዓመቱን የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም እየገመገሙ ነው። በዚሁ ወቅት ሚኒስትሩ፤ በኦንላይን ንግድ ምዝገባና ፈቃድ ለ2 ነጥብ 6 ሚሊየን ተገልጋዮች አገልግሎት መሰጠቱን እና 2 ነጥብ 2 ሚሊየን …

ከወጪ ንግድ 4 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ገቢ ተገኝቷል- ካሣሁን ጎፌ (ዶ/ር) Read More »

የህንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት መስክ መሰማራት እንደሚፈልጉ ገለጹ

የህንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት መስክ የመሰማራት ፍላጎት እንዳላቸው አስታወቁ። በህንድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምክትል ሚሲዮን መሪ አምባሳደር ሞላልኝ አስፋው ከህንዱ ፒኤችዲ የንግድ እና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት እና ኬኤልጂ ግሩፕ ኦፍ ኢንዱስትሪስ ከተሰኘው አምራች ኩባንያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ሽሪ ሄርማንት ጃን ጋር ተወያይተዋል። ውይይቱ የኢትዮጵያ እና ህንድ የንግድና ኢንቨስትመንት ትስስር ማጠናከር ላይ ያተኮረ ነው። አምባሳደር ሞላልኝ የኢትዮጵያን …

የህንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት መስክ መሰማራት እንደሚፈልጉ ገለጹ Read More »

የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደት እንዲሳካ እየተሰራ ነው – ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)

የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደት በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲሳካ እየተሰራ ነው ሲሉ የዓለም ንግድ ድርጅት ብሔራዊ የድርድር ኮሚቴ ዋና ተደራዳሪ የሆኑት የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትር ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) ገለጹ። የዓለም ንግድ ድርጅት ብሔራዊ የድርድር ኮሚቴ ከአባል ሀገራት ጋር በሚደረጉ የሁለትዮሽ የንግድ ስምምነቶች እንዲሁም የ6ኛው የዓለም ንግድ ድርጅት የሥራ ቡድን ስብሰባ የዝግጅት ሥራዎች የሚመክር ስብሰባ …

የኢትዮጵያ የዓለም ንግድ ድርጅት አባልነት ሂደት እንዲሳካ እየተሰራ ነው – ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) Read More »

የግሪክ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት መስክ እንዲሰማሩ ተጠየቀ

የግሪክ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ያሉ ምቹ የኢንቨስትመንት እድሎችን ተጠቅመው በዘርፉ እንዲሰማሩ ጥሪ ቀርቧል። የኢትዮ-ግሪክ የቢዝነስና ኢንቨስትመንት ፎረም በግሪክ አቴንስ ተካሂዷል። ፎረሙን ያዘጋጁት በሮም የኢትዮጵያ ኤምባሲ፣ በግሪክ የኢትዮጵያ ቆንስላ እና የግሪክ አፍሪካ ንግድ ምክር ቤት በጋራ በመተባበር ነው። በፎረሙ ላይ የኢትዮጵየ እና የግሪክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተወካዮች፣ የተለያዩ የመንግስት ተቋማት፣ የኢትዮጵያና የግሪክ የንግድ ማህበረሰብ አባላት ተሳትፈዋል። የኢፌዴሪ …

የግሪክ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት መስክ እንዲሰማሩ ተጠየቀ Read More »

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሻርጃ ከተማ አዲስ በረራ ሊጀምር ነው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ተባበሩት ዓረብ ኤምሬቶች ሻርጃ ከተማ ከግንቦት 24 ቀን 2017 ጀምሮ የመንገደኞች የበረራ አገልግሎት ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታወቀ። በሳምንት አራት ጊዜ የሚደረገው ይህ የበረራ አገልግሎት፤ መንገደኞች ወደ ሻርጃ ከተማ በተቀላጠፈ አማራጭ በቀላሉ እንዲጓዙ የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ በመካከለኛው ምሥራቅ ከ17 በላይ መዳረሻዎች እንዳሉት እና ከ100 በላይ ሳምንታዊ የመንገደኞችና የካርጎ አገልግሎት …

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሻርጃ ከተማ አዲስ በረራ ሊጀምር ነው Read More »

ኢትዮጵያና እስራኤል ያላቸውን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር ይገባል – አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር

ኢትዮጵያና እስራኤል በንግድና ኢንቨስትመንት ያላቸውን ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር መስራት እንደሚገባ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ገለጹ። አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር በኡዝቤኪስታን እየተካሄደ ከሚገኘው 150ኛው የኢንተር ፓርላሜንታሪ ኅብረት/አይፒዩ/ መድረክ ጎን ለጎን በሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ ከእስራኤል የፓርላማ ቡድን አባላት ጋር ተወያይተዋል። አቶ አገኘሁ ኢትዮጵያና እስራኤል ዘመናትን የተሻገረ መልካም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዳላቸው ጠቅሰው በንግድ፣ በኢንቨስትመንትና በቱሪዝም መስክ …

ኢትዮጵያና እስራኤል ያላቸውን የንግድና ኢንቨስትመንት ግንኙነት የበለጠ ማጠናከር ይገባል – አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር Read More »