Nexara

በሚያዝያ ወር ብቻ ከ51 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ

በሚያዝያ ወር 2016 ዓ.ም ብቻ ከ51 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በሚያዝያ ወር 51 ነጥብ 51 ቢሊየን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ 51 ነጥብ 07 ቢሊየን ብር ወይም የእቅዱን 99 ነጥብ 16 በመቶ መሰብሰብ መቻሉን የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ በሰጡት መግለጫ ገልጸዋል፡፡ ሚኒስትሯ ገቢው ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ10 ነጥብ 65 በመቶ …

በሚያዝያ ወር ብቻ ከ51 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ተሰበሰበ Read More »

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለአምራች ኢንዱስትሪው 30 ቢሊየን ብር ብድር መስጠቱን ገለጸ

ባለፉት ዘጠኝ ወራት 30 ቢሊየን ብር ለአምራች ኢንዱስትሪው ብድር መስጠቱን የኢትዮጵያ ልማት ባንክ አስታወቀ። የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በበኩሉ ከሚሰጠው ብድር 50 በመቶ የሚሆነው ለኢንዱስትሪዎች መሆኑን አስታውቋል። ከኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ጎን ለጎን “የግል ኢንቨስትመንት እና አስቻይ ሁኔታዎች” በሚል የፓናል ውይይት ተካሂዷል። የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዮሐንስ አያሌው(ዶ/ር) በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ባንኩ መንግሥት ቅድሚያ በሚሰጣቸው የትኩረት መስኮች …

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ለአምራች ኢንዱስትሪው 30 ቢሊየን ብር ብድር መስጠቱን ገለጸ Read More »

ለአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ውጤታማነት የግሉ ዘርፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ማቅረብ እንደሚጠበቅበት ተገለጸ

ለአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ውጤታማነት የግል ኩባንያው ዘርፍ ደረጃውን የጠበቀ ምርትና አገልግሎት ማቅረብ እንደሚጠበቅበት ተመላከተ። የኩባንያዎች ዝግጁነት ለአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና በሚል መሪ ሐሳብ የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ያዘጋጀው የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው። የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት መሰንበት ሸንቁጤ በመድረኩ ላይ ባደረጉት ንግግር÷ የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ለኢትዮጵያ የንግድ ማደግ ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳለው …

ለአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጣና ውጤታማነት የግሉ ዘርፍ ደረጃውን የጠበቀ አገልግሎት ማቅረብ እንደሚጠበቅበት ተገለጸ Read More »

አዳዲስ የነዳጅ ኩባንያና የነዳጅ ማደያ መገንባት እንዲቆም የተላለፈው ውሳኔ ክትትል እንዲደረግበት ተወሰነ

አዳዲስ የነዳጅ ኩባንያ እና የነዳጅ ማደያ መገንባት እንዲቆም ቀደም ሲል በተወሰነው ውሳኔ መሰረት አፈጻጸሙ ክትትል እንዲደረግበት ኮሚቴው ውሳኔ አሳልፏል። ብሔራዊ የነዳጅ ሪፎርም እስቲሪንግ ኮሚቴ ባለፉት 10 ወራት የነበረውን የነዳጅ ሪፎርም አፈጻጸም በመገምገም የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳልፏል። ባለፉት 10 ወራት በታቀደው መሰረት ስራዎች መሰራታቸውን የተመለከተው ኮሚቴው በዲጂታል የነዳጅ ግብይት የሚካሄደውን መረጃ በማዕከል ለማደራጀት እየተጠና ያለው ሲስተም ልማት …

አዳዲስ የነዳጅ ኩባንያና የነዳጅ ማደያ መገንባት እንዲቆም የተላለፈው ውሳኔ ክትትል እንዲደረግበት ተወሰነ Read More »

ከ1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በሚልቅ ወጪ የተገነቡ ፋብሪካዎች ሥራ ጀመሩ

 በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከ1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በሚልቅ ወጪ የተገነቡ ፋብሪካዎች ተመርቀው ወደ ምርት መግባታቸው ተገለጸ፡፡ “የኢትዮጵያ ታምርት፣ እኛም እንሸምት” 3ኛ ዙር ንቅናቄ በድሬዳዋ ከተማ ተጀምሯል፡፡ ንቅናቄውን ምክንያት በማድረግም የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል እና የድሬዳዋ አሥተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር ፋብሪካዎቹን መርቀው ሥራ አስጀምረዋል፡፡ ፋብሪካዎቹም የከባድ መኪና ተሳቢ ማምረቻ፣ የባለ ሦስትና አራት እግር የመኪና መገጣጠሚያ፣ …

ከ1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በሚልቅ ወጪ የተገነቡ ፋብሪካዎች ሥራ ጀመሩ Read More »

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያውያን ላይ የቪዛ ገደብ ለምን ጣለ?

የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ለኢትዮጵያ ዜጎች ቪዛ አሰጣጥ ላይ ገደብ መጣሉን አስታወቀ ህብረቱ መደበኛው ቪዛ ለማግኘት የሚጠበቀው የ15 ቀን ጊዜ ወደ 45 ቀን አራዝሞታል የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ለኢትዮጵያውያን ዜጎች ቪዛ የመስጠትን ሂደት ላይ ጊዜያው ገደቦችን ማስቀመጡን በዛሬው እለት አስታውቋል። ህብረቱ በዛሬው እለት በሳለፈው ውሳኔ የህብረቱ ለአባል ሃገራት ከዚህ በኋላ ኢትዮጵያውያን ቪዛ አመልካቾች ቪዛ ሲፈልጉ …

የአውሮፓ ህብረት በኢትዮጵያውያን ላይ የቪዛ ገደብ ለምን ጣለ? Read More »

የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ከ2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ አገኘ

የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከተጓዦችና የጭነት አገልግሎት ከ2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ። ማኅበሩ በየቀኑ ከ7 መቶ እስከ 1ሺህ ሰዎችን የማጓጓዝ አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን÷ ባለፉት ዘጠኝ ወራትም ከ155 ሺህ በላይ ተጓዦችን እና 1 ነጥብ 4 ሚሊየን ቶን የጭነት አገልግሎት በማጓጓዝ የዕቅዱን 98 በመቶ ማሳካት መቻሉን የማኅበሩ ዋና ሥራ …

የኢትዮ-ጅቡቲ ምድር ባቡር ከ2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ አገኘ Read More »

ኢትዮጵያ የ”ኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ” አባል ለመሆን እየሰራች መሆኑ ተገለጸ

ኢትዮጵያ የብሪክስ ባንክ በሆነው “ኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ” አባል ለመሆን እየሰራች መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ነብዩ ተድላ÷ በመዲናዋ በቅርቡ ጉብኝት ያደረጉት የተመድ ምክትል ዋና ፀሀፊ አሚና መሃመድ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታዬ አጽቀስላሴ ጋር ተገናኝተው በባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አንስተዋል። የፊታችን ሐምሌ ወር ኢትዮጵያ 4ኛውን ፋይናንስ ለልማት ኮንፈረንስ በተሳካ …

ኢትዮጵያ የ”ኒው ዴቨሎፕመንት ባንክ” አባል ለመሆን እየሰራች መሆኑ ተገለጸ Read More »

የአገር ውስጥ በረራ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው እንደገለጹት እየተጠናቀቀ ባለው በጀት አመት የአገር ውስጥ ተጓጓዦች ቁጥር 3.5 ሚሊየን ይደርሳል፤ ይህ መጠን ከ2015 በጀት አመት አንጻር የ34.6 በመቶ ጭማሪ የሚኖረው ነው። በቀደመው አመት በአገር ውስጥ በረራ የተስተናገዱት ተሳፋሪዎች 2.6 ሚሊየን እንደነበሩ አቶ መስፍን አስታውሰዋል። አየር መንገዱ እየሰፋ ያለውን የደንበኞች ቁጥር ታሳቢ በማድረግ የቦሌ አለምአቀፍ …

የአገር ውስጥ በረራ በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መሆኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ አስታወቀ Read More »

የኢትዮ-ፓኪስታን የቢዝነስ መድረክ የተመለከተ ውይይት በላሆር ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ተካሄደ

በፓኪስታን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከላሆር ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጋር በመተባበር የንግዱን ማህበረሰብ ተሳትፎ ለማበረታታት የኢትዮ-ፓኪስታን የቢዝነስ መድረክ አዘጋጅቷል። ኢስላማባድ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስተባባሪነት የሚዘጋጀው የቢዝነስ መድረክ ከፈረንጆቹ ግንቦት 26 እስከ 31 ቀን 2024 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተጠቁሟል። በርካታ ቁጥር ያላቸው የንግዱ ማህበረሰብ በኢትዮ-ፓኪስታን የቢዝነስ መድረክ ላይ ከማኑፋክቸሪንግ፣ ጨርቃጨርቅ፣ ማዳበሪያ፣ መድሀኒት፣ ህክምና፣ ግብርና፣ ኬሚካል፣ ግንባታ፣ ቱሪዝም …

የኢትዮ-ፓኪስታን የቢዝነስ መድረክ የተመለከተ ውይይት በላሆር ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ተካሄደ Read More »