OneStop

የአፍሪካ የንግድ ፋይናንስን ለማሳደግ የሚያስችል 300 ሚሊየን ዶላር ብድር ከቻይና ተገኘ

የአፍሪካ ፋይናንስ ኮርፖሬሽን ከቻይና ኤክስፖርትና ኢምፖርት ባንክ ጋር የ300 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነት መፈራረሙን አስታውቋል። ስምምነቱ በግብፅ ከእስያ መሠረተ ልማት ኢንቨስትመንት ባንክ ዓመታዊ ስብሰባዎች ጎን ለጎን እንደተፈረመ ነው የተነገረው። ብድሩ በአፍሪካና በቻይና መካከል ያለውን የጥሬ ዕቃና የአገልግሎት ዘርፍን የበለጠ በማሳለጥ በአፍሪካ ውስጥ የንግድ ፋይናንስና ኢንቨስትመንትን ለመደገፍ ወሳኝነት እንዳለው ተገልጿል። በተጨማሪም በአፍሪካ እየጨመረ ያለውን የንግድ ፋይናንስና …

የአፍሪካ የንግድ ፋይናንስን ለማሳደግ የሚያስችል 300 ሚሊየን ዶላር ብድር ከቻይና ተገኘ Read More »

አየር መንገዱ ወደ ቻይና ጓንዡ የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ ወደ 10 አሳደገ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከመስከረም 30 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ቻይና ጓንዡ የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ ወደ 10 ማሳደጉን አስታወቀ። አየር መንገዱ ከዚህ በፊት የነበረው ሰባት ሳምንታዊ በረራ ላይ ሶስት ሳምንታዊ በረራ መጨመሩን አስታውቋል። ይህም አየር መንገዱ ወደ ከተማዋ የሚያደርገውን ሳምንታዊ በረራ ወደ 10 ከፍ እንደሚያደርገው ከአየር መንገዱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ከ20 ቢሊየን ብር በላይ ብድር ለመስጠት መዘጋጀቱን ገለጸ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በ2016 በጀት ዓመት ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች ከ20 ቢሊየን ብር በላይ ብድር ለመስጠት ዕቅድ መያዙን አስታወቀ። ባንኩ ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ሥልጠና በመስጠት እና በብድር የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ ኢንተርፕራይዞች ለአገር ልማት የላቀ ሚና እንዲወጡ እየሰራ መሆኑንም ገልጿል፡፡ እስካሁንም በአራት ዙር የሰጠውን የሥልጠና መስፈርት አሟልተው የብድር ጥያቄ ላቀረቡ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች 20 ቢሊየን …

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለአነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ከ20 ቢሊየን ብር በላይ ብድር ለመስጠት መዘጋጀቱን ገለጸ Read More »

በኦንላይን ከ400 ሺህ በላይ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ተሰጠ

ሶስት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከ400 ሺህ በላይ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት በኦንላይን መስጠቱን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታወቀ። ሚኒስቴሩ ከሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት አሰጣጡን በሀገር አቀፍ ደረጃ በኦንላይን ማድረጉ ይታወሳል። ከሐምሌ 1 ቀን 2015 ዓ.ም እስከ መስከረም 8 ቀን 2016 ዓ.ም ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ 401 ሺህ 830 …

በኦንላይን ከ400 ሺህ በላይ የንግድ ምዝገባና ፈቃድ አገልግሎት ተሰጠ Read More »

ማማ ዱይንግ ጉድ የሴቶችን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ከሁዋዌይ ጋር እየሰሩ ነው

በኬንያ ቀዳማዊት እመቤት ራቼል ሩቶ የሚመራው ‘ማማ ዱይንግ ጉድ’ የተባለው ድርጅት ሴቶችን በዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማብቃት ከሁዋዌይ ጋር ጥምረት ፈጥሮ እየሰራ ነው። ድርጅቱ ከ14 ሺህ በላይ የሚሆኑ የኬንያ ሴቶች ማኅበራትን በዲጂታል ክህሎት ትምህርት ተደራሽ ለማድረግ ከሁዋዌይ ኬንያ ጋር የመግባቢያ ሠነድ ተፈራርሟል። በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የ ”ማማ ዱይንግ ጉድ” ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዶክተር ጆን ቹሞ …

ማማ ዱይንግ ጉድ የሴቶችን የቴክኖሎጂ ተጠቃሚነት ለማሳደግ ከሁዋዌይ ጋር እየሰሩ ነው Read More »

በዩናይትድ ስቴትስ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ከፍተኛ ልምድ ያለው ኢስተርን ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ኃላፊ አቶ ፍጹም ከተማ እና የአሜሪካ ምስራቃዊ ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ ዴቪድ ሃም እና የልኡካን ቡድኑን ውይይት ለማድረግ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል። በውይይቱ ላይ አቶ ፍፁም የአሜሪካ ኢስተርን ኮርፖሬሽን በቂሊንጦ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ላይ ኢንቨስት ለማድረግ ያለውን ፍላጎት አድንቀዋል።በኢንዱስትሪ ፓርኮች ያለውን የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት ለማሳደግ ኮርፖሬሽኑ የማሻሻያ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን አቶ ፍጹም ጠቅሰዋል። …

በዩናይትድ ስቴትስ በኮንስትራክሽን ዘርፍ ከፍተኛ ልምድ ያለው ኢስተርን ኮርፖሬሽን በኢትዮጵያ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ Read More »