OneStop

የታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል

የታህሳስ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል ተብሏል። የሁሉም የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ከኅዳር 26 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ባለበት እንደሚቀጥል የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል። ቀደም ሲል የነበረው የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ስንት ነው ? ምንጭ፦ የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር

አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከ3 ነጥብ 8 ሚሊየን ኩንታል በላይ የቡና ምርት መሰብሰቡን አስታወቁ

በ2016 የምርት ዘመን 11 ነጥብ 5 ሚሊየን ኩንታል የቡና ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱን እና እስካሁን ከ3 ነጥብ 8 ሚሊየን ኩንታል በላይ መሰብሰቡን የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ አስታወቁ፡፡ አፈፃፀሙ በምርት መጠንና ፍጥነት የተቀመጡት ግቦች እየተሳኩ መሆናቸውን ያመለክታል ሲሉ ርዕሰ መስተዳድሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡ ከግብርናው ዘርፍ ዓላማዎች አንዱ የወጪንግድን ማሳደግ መሆኑን ጠቁመው ÷ ይህንን ግብ …

አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከ3 ነጥብ 8 ሚሊየን ኩንታል በላይ የቡና ምርት መሰብሰቡን አስታወቁ Read More »

በዱባይ የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት አቅም ለማስተዋወቅ ያለመ የቢዝነስ ፎረም ተካሄደ

በዱባይ እየተካሄደ ካለው 28ኛው ዓለም አቀፉ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ጎን ለጎን የኢትዮጵያን እምቅ የኢንቨስትመንት አቅም ለማስተዋወቅ ያለመ የቢዝነስ ፎረም ተካሄዷል፡፡ በዚህ ፎረም ላይ በተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የሚገኙና በኢትዮጵያ የመሰማራት አቅም ያላቸው ከ30 በላይ ኩባንያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ እያስመዘገበች ስላለው ስኬት፣ በዘርፉ የግል ባለሀብቶች ሚና …

በዱባይ የኢትዮጵያን የኢንቨስትመንት አቅም ለማስተዋወቅ ያለመ የቢዝነስ ፎረም ተካሄደ Read More »

የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ወደ ካዛብላንካ የጭነት ማጓጓዝ በረራ ሊጀምር ነው

የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ ወደ ሞሮኮ – ካዛብላንካ አዲስ የጭነት ማጓጓዝ በረራ ለመጀመር ዝግጅት ማጠናቀቁን አስታውቋል። ወደ ካዛብላንካ የሚያርገው የጭነት በረራ በሰሜን አፍሪካ የመጀመሪያው መሆኑን የኢትዮጵያ ዓየር መንገድ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል። ወደ ካዛብላንካ የሚደረገውን የጭነት በረራ ጨምሮም ዓየር መንገዱ በአፍሪካ የሚያደርጋቸው የጭነት በረራዎች ቁጥር ወደ 34 ከፍ ማለቱ ተገልጿል። ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ

 የሙያ ደኅንነትና ጤንነትን ለመጠበቅ አዲስ የአሠራር ሥርዓት እየተዘረጋ ነው

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሙያ ደኅንነትና ጤንነት ዴስክ ኃላፊ ጥዑመእዝጊ በርሄ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ መከላከልን መሰረት ያደረገ አጠቃላይ የሙያ ደኅንነትና ጤንነትን ማስጠበቅ የሚያስችል አዲስ አሠራር እየተዘረጋ ነው። የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አጠቃላይ የሥራ ላይ ደኅንነትን ከማረጋገጥ አኳያ ከ12 ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጋር የጎንዮሽ የመግባቢያ ስምምነት መፈራረሙን ገልጸው፤ ስምምነቱ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶቹ ከዚህ በፊት ያልነበራቸው የየራሳቸው ፖሊሲ …

 የሙያ ደኅንነትና ጤንነትን ለመጠበቅ አዲስ የአሠራር ሥርዓት እየተዘረጋ ነው Read More »

ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የቡና ንግድ ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር እንደምትፈልግ ገለጸች

ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የቡና ንግድ ትስስር ይበልጥ ማጠናከር እንደምትፈልግ የሀገሪቱ ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲ የግብርናና የገጠር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዱ ጂሃኦ ገለጹ። በቻይና ብሔራዊ ኮንግረስ ፓርቲ የግብርናና የገጠር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ሎሚ በዶና ሌሎች የምክር ቤት አባላት ገላን የሚገኘውን ኤ ኤም ጂ ቡና ላኪ ድርጅትን ጎብኝተዋል። ዱ …

ቻይና ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን የቡና ንግድ ትስስር ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር እንደምትፈልግ ገለጸች Read More »

ኤም ቲ ኤን  በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ

የተርኪዬው ኤም ቲ ኤን ኢንተርናሽናል መንግስታዊ ኩባንያ በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ። በተርኪዬ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር እና ልዩ መልዕክተኛ አደም መሐመድ ኤም ቲ ኤን ኢንተርናሽናል ኩባንያ ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ኒል ይለድሪም እና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱም የኩባንያው ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ኒል ይልድሪም ተርክዬ እና ኢትዮጵያ በማዕድን ዘርፍ በጋራ …

ኤም ቲ ኤን  በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፍ ለመሰማራት ፍላጎት እንዳለው ገለጸ Read More »