Nexara

የእስራኤል ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ ቀረበ

የእስራኤል ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር ተስፋዬ ይታይህ ጥሪ አቀረቡ። በእስራኤል ለሚገኙ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ስላለው ኢንቨስትመንት የማስተዋወቂያ መርሃ ግብር የተካሄደ ሲሆን÷በዚሁ መርሐ ግብር ላይ ባለሃብቶች፣ የኩባንያ ሃላፊዎችና የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል በመድረኩ አምባሳደር ተስፋዬ ÷ ኢትዮጵያ በግብርና፣ በአግሮ-ፕሮሰሲንግ፣ በኢንዱስትሪ ልማት፣ በማዕድን ማምረት እና በጤና ዘርፎች ያላትን ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጮች አብራርተዋል። መንግስት ለኢንቨስትመንት ከሰጠው …

የእስራኤል ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ ቀረበ Read More »

የሠነደ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ ለኢትዮጵያ ስታርት አፖች እድገት የተሻለ እድል ይፈጥራል

የሠነደ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ መፈቀድ ለኢትዮጵያ ስታርት አፖች እድገት የተሻለ ዕድል ይዞ መምጣቱን የኢትዮጵያ ሠነደ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ አስታወቀ። የኢትዮጵያ ሠነደ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ጥላሁን እስማዔል ለኢዜአ እንዳሉት ካፒታል ገበያና ስታርትአፕ ተመጋጋቢ ዘርፎች ናቸው። በዓለም የታወቁ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ከጀማሪ ስራ ፈጣሪነት እንደተነሱ በማውሳት፣ ከዛሬ ቁመናቸው እንዲደርሱ ምቹ ሁኔታዎች እንደተፈጠረላቸው አንስተዋል። …

የሠነደ ሙዓለ ነዋዮች ገበያ ለኢትዮጵያ ስታርት አፖች እድገት የተሻለ እድል ይፈጥራል Read More »

በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ለሚሳተፉ የቻይና ባለሀብቶች ትብብር ለማድረግ የሚያስችል ውይይት ተካሄደ

ከግንቦት 1 እስከ 5 በሚካሄደው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ላይ ለሚሳተፉ የቻይና ባለሀብቶች ትብብርለማድረግ የሚያስችል ምክክር ተካሂዷል። በቤጅንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከቻይና-አፍሪካ የኢኮኖሚ እና ንግድ ጉዳዮች አስተባባሪ ኮሚቴ የስራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አካሂዷል። በውይይቱ በኢትዮጵያ ቅድሚያ በሚሰጥባቸው ኢንቨስትመንት መስኮች በተለይም በንግድ እና በቱሪዝም ዘርፍ ያሉ ዕምቅ ዕድሎችን ለማስተዋወቅ የሚረዱ ፎረሞችን በጋራ በተለያዩ ከተሞች ለማዘጋጀት የሚያስችል ምክክር ተደርጓል። …

በኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ለሚሳተፉ የቻይና ባለሀብቶች ትብብር ለማድረግ የሚያስችል ውይይት ተካሄደ Read More »

30 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ከኢንተርኔት አገልግሎት ውጪ መሆናቸው ተገለጸ

ኢትዮጵያ ኢንተርኔት በመዝጋቷ ምክንያት 1 ነጥብ 6 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አጥታለች ተብሏል ዓለማችን በኢንተርኔት መዘጋት ምክንያት 9 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ማጣቷ ተገልጿል 30 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ከኢንተርኔት አገልግሎት ውጪ መሆናቸው ተገለጸ። ዓለም አቀፍ የኢንተርኔት አገልግሎቶችን በመከታተል እና ሪፖርቶችን በማውጣት የሚታወቀው ኔት ብሎክስ የ2023 ሪፖርቱን ይፋ አድርጓል። በዚህ ተቋም ሪፖርት መሰረት ኢትዮጵያ ከኢንተርኔት በመዝጋት ገቢ ካጡ ሀገራት …

30 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ከኢንተርኔት አገልግሎት ውጪ መሆናቸው ተገለጸ Read More »

የህንድ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀረበ

የህንድ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ እንዲሳተፉ በህንድ የኢትዮጵያ አምባሳደር ደመቀ አጥናፉ ጥሪ አቀረቡ። በህንድ ሙምባይ ከተማ የእስያ አፍሪካ የንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ያዘጋጀው ስድስተኛው ዓለም አቀፍ የንግድ አመራሮች ፎረም ተካሂዷል። አምባሳደሩ በፎረሙ ላይ እንደገለጹት÷ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የግብርና፣ የማምረቻ፣ የማዕድን፣ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና ቱሪዝም ዘርፎች ቅድሚያ የሚሰጣቸው የኢንቨስትመንት መስኮች ናቸው። በኢትዮጵያ በኢንቨስትመንት …

የህንድ ኩባንያዎች በኢትዮጵያ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ቀረበ Read More »

የኢትዮጵያ ስታርት አፕ ዐውደ-ርዕይ ተከፈተ

 570 ስታርት አፖች የሚሳተፉበት የኢትዮጵያ ስታርት አፕ ዐውደ-ርዕይ በሣይንስ ሙዚየም ተከፈተ። ለሦስት ሣምንታት በሚቆየው ዐውደ-ርዕይ ላይ÷ የመጀመሪያ ደረጃ፣ የመጀመሪያ ደረጃን የተሻገሩ እና ወደገበያ የመቀላቀል ደረጃ ላይ የደረሱ ስታርት አፖች  ሥራዎቻቸውን አቅርበዋል። የሥራ እና ክኅሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃያት ካሚል፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ/ር)፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የገንዘብ ሚኒስትር ዴዔታ ኢዮብ ተካልኝ (ዶ/ር) እና ሌሎች …

የኢትዮጵያ ስታርት አፕ ዐውደ-ርዕይ ተከፈተ Read More »

አየር መንገዱ ወደ አንጎላ ሉዋንዳ ከተማ ዕለታዊ በረራ ጀመረ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አንጎላ ሉዋንዳ ከተማ የሚያደርገውን በረራ ዕለታዊ ማድረጉን አስታወቀ። ወደ አንጎላ ሉዋንዳ ከተማ ሲደረግ የነበረው ሳምንታዊ በረራ በየዕለቱ እንዲሆን መደረጉ መንገደኞች የተመቸ የጉዞ አማራጭ እንዲኖራቸው እንደሚያስችል አየር መንገዱ አስታውቋል።

የቻይናው ሲኢኢሲ ኩባንያ በኢትዮጵያ በተለያዩ ኢንቨስትመንቶች መሰማራት እፈልጋለሁ አለ

የቻይና ኢነርጂ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሲኢኢሲ) ኩባንያ በአዳዲስ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ግንባታ እንዲሁም በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ጋር መስራት እንደሚፈልግ ገለጸ። የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ከኩባንያውን ከፍተኛ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል። የኩባንያው ኃላፊዎችም በውይይቱ ላይ አዳዲስ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን በመገንባት፣ የግንባታ ግብዓቶችን እና የኤሌክትሪካል ቁሶችን በማምረት እንዲሁም በሌሎች የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመሰማራት …

የቻይናው ሲኢኢሲ ኩባንያ በኢትዮጵያ በተለያዩ ኢንቨስትመንቶች መሰማራት እፈልጋለሁ አለ Read More »

ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይት በሁሉም ባንኮች እንደሚጀመር አስታወቀ

በውስን የክፍያ አማራጮች ብቻ የነበረው የነዳጅ ግብይት በቀጣይ በሁሉም ባንኮች እንደሚጀመር የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል። የባለስልጣኑ የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር በቀለች ኩማ እንዳሉት÷ ከነዳጅ ግብይትጋር በተያያዘ በተገልጋዮችና ሌሎች ባንኮች የሚነሱ ቅሬታዎችን ለመፍታት አገልግሎቱን ማስፋት አስፈልጓል። በዚህ መሰረትም በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ በኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ እና በቴሌ ብር ብቻ ሲደረግ የነበረው የነዳጅ ግብይት ዲጂታል የክፍያ አማራጮችን በማስፋት ሌሎች …

ባለስልጣኑ የነዳጅ ግብይት በሁሉም ባንኮች እንደሚጀመር አስታወቀ Read More »

ሁዋዌ የቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ኩባንያ የፋይናንስ ዘርፉን በዲጂታል ለማገዝ ያለመ መድረክ እያካሄደ ነው

 ሁዋዌ የቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ኩባንያ የፋይናንስ ዘርፉን በዲጂታል ለማገዝ ያለመ መድረክ እያካሄደ ይገኛል። ተቋሙ በኢትዮጵያ የዲጂታል ሳምንት መርሀ ግብር ካለፉት ቀናት ጀምሮ ሲያካሂድ ቆይቷል። የኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን የ2025 ዕቅድን እውን ለማድረግ ብሎም የፋይናንስ ዘርፉን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ የዲጂታል ሳምንቱ አስቻይ ሁኔታን የሚፈጥር እንደሆነ ተመላክቷል። መድረኩ የዲጂታል ፋይናንስ ስርዓቱ የዘመነ እንዲሆንና ደህንነቱ የተጠበቀ የፋይናንስ አገልግሎት እንዲኖር የሚያግዝ እንደሆነ …

ሁዋዌ የቴክኖሎጂ ኢንፎርሜሽን ኩባንያ የፋይናንስ ዘርፉን በዲጂታል ለማገዝ ያለመ መድረክ እያካሄደ ነው Read More »