Nexara

ሁለት ዘመናዊ የአውሮፕላን መለዋወጫና ጥገና ማዕከላት ወደ ሥራ ሊገቡ ነው

 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ተጨማሪ ሁለት ዘመናዊ የአውሮፕላን መለዋወጫና ጥገና ማዕከላትን ወደ ሥራ ሊያስገባ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ጣሰው ገለጹ። የአፍሪካ አቪዬሽን የአውሮፕላን መለዋወጫና ጥገና ተቋማት ኮንፍረንስና ኤግዚቢሽን ትላንት በአዲስ አበባ ተከፍቷል። ዋና ሥራ አስፈጻሚው አቶ መስፍን ጣሰው በመድረኩ ላይ እንደገለጹት፤ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት መጨረሻ ተጨማሪ ሁለት ዘመናዊ የአውሮፕላን መለዋወጫና ጥገና ማዕከላትን …

ሁለት ዘመናዊ የአውሮፕላን መለዋወጫና ጥገና ማዕከላት ወደ ሥራ ሊገቡ ነው Read More »

የቻይናው ዘኒት ስቲል ኩባንያ በኢትዮጵያ ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት አለኝ አለ

 በቻይና ብረታብረቶችንና የኤሌክትሪክ መሣሪያዎችን አምራቹ ዘኒት ስቲል ኩባንያ በኢትዮጵያ በተለያዩ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳለው ገልጿል። የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈፃሚ አክሊሉ ታደሰ ከኩባንያው የስራ ኃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል። በውይይታቸውም በኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ በርካታ ቻይናውያን ባለሃብቶች መኖራቸውን ተከትሎ ኮርፖሬሽኑ የቻይና ኢንቨስትመንት ዴስክ ከፍቶ እየሰራ መሆኑን አቶ አክሊሉ አስረድተዋል። የኩባንያው ኃላፊዎችም÷ ስለ ኢንቨስትመንት ዕቅዱ …

የቻይናው ዘኒት ስቲል ኩባንያ በኢትዮጵያ ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት አለኝ አለ Read More »

አቶ አሕመድ ሺዴ ከአሜሪካ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር መከሩ

የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴ ከተለያዩ የአሜሪካ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል። የ2024 የዓለም ባንክ እና አይኤም ኤፍ ስብሰባዎች ጎን ለጎን በሚኒስትር አሕመድ ሺዴ የሚመራው ልዑክ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት አምባሳደር ሞሊ ፊ፣ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ አምባሳደር ማይክል ሀመር እና የአሜሪካ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ግምጃ ቤት ምክትል ፀሐፊ …

አቶ አሕመድ ሺዴ ከአሜሪካ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር መከሩ Read More »

የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪትን የአሰራርና የቁጥጥር ስርዓር ማዘመን እንደሚገባ ተጠቆመ

የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል እና የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት ስርዓትን በጋራ ማሳለጥ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል። በውይይታቸውም ዜጎች ደህንነቱ የተረጋገጠ የውጭ ሀገር ሥራ ስምሪት እንዲያገኙና መብትና ተጠቃሚነታቸው እንዲረጋገጥ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የተጀምሩ ሥራዎችን ተመልክተዋል። በዘርፉ የተደረገውን ሪፎርም ተከትሎ ዜጎች መብትና ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ሁሉም አስፈፃሚ አካላት በጋራ እየሰሩ …

የውጭ ሀገር የሥራ ስምሪትን የአሰራርና የቁጥጥር ስርዓር ማዘመን እንደሚገባ ተጠቆመ Read More »

በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከGrand World Investment Holding Group ኩባንያ ፕሬዚዳንት ጋር ውይይት አደረገ

በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምክትል መሪ ክቡር አምባሳደር ደዋኖ ከድር ከGrand World Investment Holding Group ኩባንያ ፕሬዚዳንት Mr. Wenguang Liu ጋር በኢትዮጵያ በማኑፋክቸርንግ መስክ ኢንቨስት በሚያደርጉበት ሁኔታ ላይ ውይይት አካሂደዋል። ኩባንያው በመስኩ በተለይም በፋርማሲውቲካል፣ በአግሮ-ፕሮሰስንግ፣ በኤልክትሪክ መኪኖች መገጣጠም እና ቻርጂንግ ስቴሽኖች በመዘርጋት መስክ በኢትዮጵያ ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ፕሬዚዳንቱ የገለጹ ሲሆን፣ ከግንቦት 1 እስከ 5 አዲስ …

በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከGrand World Investment Holding Group ኩባንያ ፕሬዚዳንት ጋር ውይይት አደረገ Read More »

የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ 28 ሚሊየን ዶላር ዋጋ ያላቸው ምርቶችን ለውጭ ገበያ አቀረበ

ባለፉት ዘጠኝ ወራት የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከ28 ሚሊየን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸው ምርቶችን ለውጭ ገበያ ማቅረቡን አስታወቀ። በሌላ በኩል ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከ850 ለሚልቁ ወገኖች አዲስ የሥራ ዕድል መፈጠሩን የፓርኩ ሥራ አስኪያጅ አሕመድ ሰዒድ ገልፀዋል። እንዲሁም በውጪ ምንዛሪ ወደ ሀገር የሚገቡ ምርቶችን ለማስቀረት በሚደረገው ጥረት ተኪ ምርቶችን በማምረት ፓርኩ ከ350 ሺህ ዶላር በላይ ማዳን መቻሉን …

የኮምቦልቻ ኢንዱስትሪ ፓርክ 28 ሚሊየን ዶላር ዋጋ ያላቸው ምርቶችን ለውጭ ገበያ አቀረበ Read More »

የብድር ሁኔታ በተመለከተ ያለው ማዕቀፍ በፍጥነት ስለሚሻሻልበት ሁኔታ ምክክር ተደረገ

የብድር ሁኔታ በተመለከተ ያለው ማዕቀፍ በፍጥነት ስለሚሻሻልበትና የብድር እፎይታ ሂደትን ስለሚሰጥበት ሁኔታ ምክክር ተደረገ። የቡድን 20 የወቅቱ ፕሬዚዳንት የሆነችው ብራዚል፣ የዓለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም (አይኤምኤፍ) እና የዓለም ባንክ በትብብር ያዘጋጁት የዓለም ዓቀፍ የሀገራት የብድር ውይይት መድረክ ላይ ተካሂዷል። በመድረኩ 22 አባላት ያሉት የፓሪስ ክለብ ሀገራት፣ የፓሪስ ክለብ አባል ያልሆኑ አበዳሪ ሀገራት፣ ተበዳሪ ሀገራት እና የግሉ …

የብድር ሁኔታ በተመለከተ ያለው ማዕቀፍ በፍጥነት ስለሚሻሻልበት ሁኔታ ምክክር ተደረገ Read More »

ምርጥ 10 የአፍሪካ ኤርፖርቶች የትኞቹ ናቸው?

የደቡብ አፍሪካ ኤርፖርቶች ከአንደኛ እስከ ሶስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል የኢትዮጵያው ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት ከአፍሪካ በሰባተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል ምርጥ 10 የአፍሪካ ኤርፖርቶች የትኞቹ ናቸው? ስካይትራክስ የተሰኘው የአቪዮሽን መረጃዎችን በማውጣት የሚታወቀው ተቋም ሪፖርቱን አውጥቷል። የ2024 ምርጥ የአፍሪካ ኤርፖርቶች ይፋ በተደረጉበት በዚህ ሪፖርት መሰረት ኬፕታወን ኤርፖርት የዓመቱ ምርጥ አንደኛ ተብሎ ተመርጧል። ደርባን ኪንግ ሻካ እና ጆሀንስበርግ …

ምርጥ 10 የአፍሪካ ኤርፖርቶች የትኞቹ ናቸው? Read More »

በመዲናዋ 108 ቢሊየን ብር ገቢ ተሰበሰበ

የአዲስ አበባ ከተማ ገቢዎች ቢሮ ባለፉት ዘጠኝ ወራት 108 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን አስታውቋል። የቢሮው ኃላፊ አደም ኑሪ እንደገለጹት÷ቢሮው በ2016 በጀት ዓመት ባለፉት ዘጠኝ ወራት 109 ነጥብ 6 ቢሊየን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ 108 ቢሊየን ብር ሰብስቧል። ገቢው ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ45 በመቶ እድገት ወይም የ34 ቢሊየን ብር ጭማሪ ማሳየቱንም ጠቅሰዋል። ቢሮው ገቢውን …

በመዲናዋ 108 ቢሊየን ብር ገቢ ተሰበሰበ Read More »

በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዓለም አቀፍ ሰሊጥ ኮንፈሬንስ ላይ ተሳትፎ አደረገ

የሚሲዮኑ ምክትል መሪ ክቡር አምባሳደር ደዋኖ ከድር በሻንዶንግ ፕሮቪንስ በቺንዳሆ ከተማ እ.ኤ.አ ከኤፕሪል 15 እስከ 17 ቀን 2024 በተካሄደ ‘’China International Sesame Conference’’ ላይ ተሳትፎ በማድረግ የሀገራችንን የሰሊጥ ምርት አስተዋውቀዋል። ክቡር አምባሳደር ደዋኖ ከድር በኮንፈረንሱ ባደረጉት ንግግር ከሀገራችን ወደ ቻይና የሚላክ የሰሊጥ ምርት ባለፉት ጥቂት ዓመታት ቅናሽ ማሳየቱን ጠቅሰው በዚህ ዓመት በኢትዮጵያ የተመረተው የሰሊጥ ምርት …

በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ በዓለም አቀፍ ሰሊጥ ኮንፈሬንስ ላይ ተሳትፎ አደረገ Read More »