Nexara

በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተመረጡ የክሪፕቶ መገበያያዎች ምን ምን ናቸው?

ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አምስት የክሪፕቶ ከረንሲዎችን ዝርዝር ይፋ አድርገዋል። አሜሪካ በቅርቡ ዓለም አቀፍ የክሪፕቶ ግብይት ጉባኤ እንደምታዘጋጅ ተገልጿል በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተመረጡ የክሪፕቶ መገበያያዎች ምን ምን ናቸው? “ቢትኮይን የአጭበርባሪዎች ነው” በማለት የሚታወቁት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሁን ላይ ዋነኛ የክሪፕቶ ከረንሲ ወይም ምናባዊ ግብይት አቀንቃኝ ሆነዋል። ከሰሞኑ ደግሞ የአሜሪካ እና የዓለም ክሪፕቶ መገበያያ እና ሀብት መያዣ …

በፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የተመረጡ የክሪፕቶ መገበያያዎች ምን ምን ናቸው? Read More »

የጃፓን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎታቸውን ገለጹ

በጃፓን የኢትዮጵያ ኤምባሲ በተካሄደው 33ኛው የአፍሪካ፣ እስያና ዓረብ የኢንቨስትመንት ፎረም ላይ የተሳተፉ የጃፓን ባለሀብቶች ለቅድመ ኢንቨስትመንት ጥናት ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ገለጹ። ባለሀብቶቹ በኢትዮጵያ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ላይ ኢንቨስት ማድረግ እንደሚፈልጉ ማረጋገጣቸውን የኢንዱስትሪ ልማት ኮርፖሬሽን መረጃ አመላክቷል። በዚህም በኢትዮጵያ በማምረቻ፣ በንግድ፣ ሎጂስቲክ እና በሌሎች የአገልግሎት ዘርፎች ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎት እንዳላቸው ነው የተገለጸው። በቅርቡም ለቅድመ ኢንቨስትመንት ጥናት …

የጃፓን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ ኢንቨስት የማድረግ ፍላጎታቸውን ገለጹ Read More »

ኮርፖሬሽኑ የኢትዮጵያ ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖችን ፀጋ አስተዋወቀ

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በቶኪዮ እየተካሄደ በሚገኘው 33ኛው የእስያ፣ ዓረብ እና አፍሪካ የኢንቨስትመንት ፎረም ላይ የኢትዮጵያ ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖችን ፀጋ አስተዋወቀ። የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሰሐ ይታገሱ (ዶ/ር) መንግሥት የኢንቨስትመንት ዘርፉን ለውጭ ባለሀብቶች ቀልጣፋ፣ ሳቢ እና ተመራጭ ለማድረግ የወሰዳቸውን የፖሊሲ ማበረታቻዎች፣ ሀገር በቀል የሪፎርም ሥራዎችን እና በልዩ ኢኮኖሚ ዞኖቹ ውስጥ ያሉ የአንድ መስኮት አገልግሎቶችን አብራርተዋል። …

ኮርፖሬሽኑ የኢትዮጵያ ልዩ ኢኮኖሚ ዞኖችን ፀጋ አስተዋወቀ Read More »

የመጋቢት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት እንደሚቀጥል ተገለጸ

የመጋቢት ወር የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ በነበረበት እንዲቀጥል በመንግሥት መወሰኑን የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል። የነዳጅ ማደያዎችና ኩባንያዎች በነዳጅ ውጤቶች ግብይት አዋጅ እና መመሪያ መሠረት መንግስታዊ ውሳኔውን ተግባራዊ እንዲያደርጉም ሚኒስቴሩ አሳስቧል። ምንጭ፦ ኤፍ.ኤም.ሲ

አየር መንገዱ አህጉራዊ የካርጎ አገልግሎት ሽልማቶችን አገኘ

የኢትዮጵያ የካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በአፍሪካ ቀዳሚ በመሆን ሁለት ሽልማቶችን ማግኘቱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ አስታወቀ። “Aviation Achievement Awards” የተሰኘ የአቪዬሽን ዘርፍ የሽልማት መርሃ ግብር በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ዱባይ ተከናውኗል። የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት የህክምና ቁሳቁሶችን በማጓጓዝ እና አጠቃላይ በካርጎ አገልግሎት ዘርፎች ከአፍሪካ ቀዳሚ በመሆን ሽልማቶችን ማግኘቱን የአየር መንገዱ መረጃ ያመለክታል። የአፍሪካ ምርጥ የፋርማ …

አየር መንገዱ አህጉራዊ የካርጎ አገልግሎት ሽልማቶችን አገኘ Read More »

የጃፓኑ ኩባንያ በሃዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የሶላር ፓናል ማምረት ጀመረ

በሃዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን በ60 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የተለያዩ ሶላር ፓኔሎችን ለማምረት የገባው የጃፓኑ ቶዮ ሶላር ኩባንያ የማሽን ተከላ ስራዎችን በማጠናቀቅ የሙከራ ምርት ማምረት ጀምሯል። የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፍሰሃ ይታገሱ (ዶ/ር)፥ በልዩ የኢኮኖሚ ዞኑ የቶዮ ሶላር ኩባንያን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴን ጎብኝተዋል። ዋና ስራ አስፈጻሚው፥ ኩባንያው በሙሉ አቅሙ ወደ ምርት ሂደት እንዲገባ …

የጃፓኑ ኩባንያ በሃዋሳ ልዩ የኢኮኖሚ ዞን የሶላር ፓናል ማምረት ጀመረ Read More »

የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ 1 ነጥብ 54 ትሪሊየን ብር ደረሰ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ 1 ነጥብ 54 ትሪሊየን ብር መድረሱ ተገለጸ። የባንኩ ፕሬዚዳንት አቤ ሳኖ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ የሥራ ኃላፊዎች ጋር የበጀት ዓመቱን የመጀመሪያ አጋማሽ ሥራ አፈጻጸም ገምግመዋል። በበጀት ዓመቱ እስከ የካቲት 16 ቀን 2017 ድረስ የተሰበሰበው ተቀማጭ ገንዘብ ከ350 ቢሊየን ብር በላይ መድረሱን አቶ አቤ በግምገማው ላይ ገልጸዋል። አጠቃላይ የባንኩ ተቀማጭ የገንዘብ …

የባንኩ አጠቃላይ ተቀማጭ ገንዘብ 1 ነጥብ 54 ትሪሊየን ብር ደረሰ Read More »

ከ300 በላይ ኩባንያዎች የተሳተፉበት የኢትዮ-ቻይና ቢዝነስ ፎረም በቤጂንግ ተካሄደ

 በቻይና የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከኢትዮ-ቻይና የወዳጅነትና ትብብር ኮሚቴ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የቢዝነስ ፎረም በዛሬው ዕለት በቤጂንግ ተካሂዷል። በቻይና የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈራ ደርበው፤ የሁለቱን ሀገራት ሁሉን አቀፍ ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር ኤምባሲው ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን በመድረኩ ላይ ገልጸዋል። በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ከ300 በላይ የቻይና ኩባንያዎች በፎረሙ ላይ የተሳተፉ ሲሆን በኢንቨስትመንት፣ በንግድና በቱሪዝም ዘርፎች በኢትዮጵያ ያሉ ዕድሎችን በሚመለከት …

ከ300 በላይ ኩባንያዎች የተሳተፉበት የኢትዮ-ቻይና ቢዝነስ ፎረም በቤጂንግ ተካሄደ Read More »

10 በወጪ ንግድ ቀዳሚ ሀገራት

ቻይና በየአመቱ ከ3 ትሪሊየን ዶላር በላይ ዋጋ ያላቸው ምርቶችን ለውጭ ሀገራት ታቀርባለች አስሩ ቀዳሚ ምርት ላኪ ሀገራት በድምሩ 12 ትሪሊየን ዶላር የሚጠጋ ዋጋ ያላቸው ምርቶችን ወደተለያዩ ሀገራት ልከዋል የወጪ ንግድ የአንድ ሀገር የኢኮኖሚ እድገት ማሳያ ነው። ምርቶቻቸውን ለበርካታ ሀገራት በመላክ በቢሊየን ዶላር የሚያስገቡ ሀገራት የአለም የገበያ ስርአትን ይቆጣጠራሉ። በአለማችን ሁለተኛዋ ባለግዙፍ ኢኮኖሚ ሀገር ቻይና ከወጪ …

10 በወጪ ንግድ ቀዳሚ ሀገራት Read More »

የኢትዮጵያ አየር መንገድ “የአፍሪካ ምርጥ የካርጎ አገልግሎት አየር መንገድ” ዕውቅና ተቀዳጀ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ካርጎና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በኬኒያ በተካሄደው የ2025 የአየር ዕቃ ጭነት አገልግሎት ልሕቀት ሽልማት መርሐ-ግብር “የአፍሪካ ምርጥ የካርጎ አገልግሎት አየር መንገድ” በመባል ዕውቅና ተቀዳጀ። በተጨማሪም “የአፍሪካ ምርጥ የካርጎ አገልግሎት ኤርፖርት” እና “ፈጣን ዕድገት እያስመዘገበ ያለ የዓመቱ የካርጎ አገልግሎት አየር መንገድ” በመባል ተደራራቢ ዕውቅና እና ሽልማት ማግኘቱን አየር መንገዱ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ አስታውቋል። እነዚህ ሽልማቶች …

የኢትዮጵያ አየር መንገድ “የአፍሪካ ምርጥ የካርጎ አገልግሎት አየር መንገድ” ዕውቅና ተቀዳጀ Read More »