ለድጎማ ተጠቃሚ ተሽከርካሪዎች 23 ነጥብ 1 ቢለየን ብር በላይ መከፈሉን የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን አስታውቋል።
ባለሥልጣኑ በ2016 በጀት ዓመት መጀመሪያ ሩብ ዓመት÷ለነዳጅ ኮንትሮባንድ ሽያጭ ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎችን 65 በመቶ መቀነስ መቻሉን አስረድቷል።
ከተቀመጠው አሠራር ውጭ አገልግሎት በማይሰጡና ነዳጅ ሣይቀዱ የድጎማ ክፍያ ለሚጠቀሙ ተሽከርካሪዎች ትብብር በሚፈፅሙ 5 ነዳጅ ማደያዎች ላይ እርምጃ መውሰዱንም ጠቁሟል።
እስከ ባለፈው መስከረም ወር መጨረሻ ድረስም 23 ነጥብ 1 ቢሊየን ብር በላይ ለድጎማ ተጠቃሚ ተሽከርካሪዎች መከፈሉን የባለስልጣኑ መረጃ ያመላክታል።
በዚሁ መንገድ 120 ቢሊየን ብር በላይ ዋጋ ያለው የነዳጅ ግብይት የተፈጸመ ሲሆን÷የነዳጅ ስርጭት ቁጥጥርን ለማዘመን ነዳጅ ጫኝ ተሽከርካሪዎች ጂ ፒ ኤስ እንዲገጥሙ መደረጉ ተገልጿል።
ማደያ በሌለባቸው 556 ወረዳዎች አዳዲስ ማደያዎች እንዲገነቡ በተቀመጠው ዕቅድ መሰረትም በ8 ወረዳዎች አዳዲስ ማደያዎች ተገንበተው የነዳጅ ትስስር ፈቃድ ማግኘታቸው ተጠቅሷል።
ምንጭ፦ ኤፍ.ቢ.ሲ