የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ጨምሮ የግል ባንኮች በዶላር መሸጫና መግዣ ዋጋ ላይ ጭማሪ አሳይተዋል
የአንድ ዶላር የመግዣ ዋጋ ላይ ገበያ መር ስርአቱ ከመጀመሩ በፊት ከነበረበት ከ46 እስከ 51 ብር ድረስ ጭማሪ ታይቷል
ኢትዮጵያ የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአቱ ገበያ መር እንዲሆን ከወሰነች በኋላ ባንኮች በየእለቱ አዲስ የምንዛሬ ዋጋ በማውጣት ላይ ናቸው።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ነሃሴ 8 2016 የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ሲያሳውቅ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋን ትናንት ሲገዛበት ከነበረው አንድ ብር ጨምሮ 103.96 ብር አድርሶታል። መግዣው ላይም ተመሳሳይ ጭማሪ በማድረግ 114.67 ብር እየገዛ ይገኛል።
የእንግዝሊ ፓውንድ ላይ ደግሞ የሁለት ብር ጭማሪ አድርጎ በ127.73 ብር እየገዛ በ141.51 ብር እንደሚሸጥ ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ አድርጓል።
ዳሽን ባንክ ደግሞ አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ103.99 ብር ገዝቶ በ116.47 ብር በመሸጥ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።
ኦሮሚያ ባንክ ባወጣው እለታዊ የውጭ ምንዛሬ ተመን በዶላር መግዣና መሸጫ ዋጋ ላይ የትናንቱን አስቀጥሏል። አንድ ዶላርን በ103.9831 ብር እየገዛ በ119.5806 ብር እየሸጠ መሆኑን አስታውቋል።
ንብ ባንክ ደግሞ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ104.64 ብር እየተገዛ በ117.20 ብር እየተሸጠ መሆኑን ነው ባወጣው እለታዊ የምንዛሬ ተመን ይፋ ያደረገው።
ምንጭ፦ አል አይን ኒውስ