ሲልኮት የተሰኘ የፓኪስታን የንግድና ዘርፍ ማህበራትና ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ ኤክስፖርት ደረጃ የሆኑ የስፖርት ግብአቶችን ለማምረት የሚያስችል ስምምነት ከኢንቨስትመንት ኮሚሽን ጋር ተፈራረሙ።
የመግባቢያ ስምምነቱ በኢትዮጵያ የፓኪስታን አምባሳደር እንዲሁም በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር በተገኙበት የሲልኮት ንግድና ዘርፍ ማህበራት እና ኢንዱስትሪ ፕሬዝዳንት አብዱል ጋሃፎር እና በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር ሃና አርአያስላሴ መካከል ተፈርሟል።
ስምምነቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን የንግድና የኢንቨስትመንት ግንኙነት ለማጎልበት ያለውን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ምንጭ፦ ኢዜአ