የፓኪስታን ባለሀብቶች በመድኃኒትና ጨርቃጨርቅ ዘርፍ መሰማራት እንፈልጋለን አሉ

 የፓኪስታን ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ ኢንዱስትሪ ፓርኮች በመድኃኒት እና ጨርቃጨርቅ ዘርፎች ለመሠማራት እንደሚፈልጉ አስታወቁ።

ከ80 በላይ የፓኪስታን ባለሀብቶችን ያካተተ ልዑክ የቂሊንጦ፣ ቦሌ ለሚ እና አዳማ ኢንዱስትሪ ፓርኮችን የሥራ እንቅስቃሴና መሠረተ-ልማቶች ጎብኝቷል።

በጉብኝቱም በመድኃኒት፣ ጨርቃጨርቅ እንዲሁም ሌሎች የቴክኖሎጂ ምርቶችና የኢንቨስትመንት ዘርፎች ለመሰማራት እንደሚፈልግ ማሳወቁን የኮርፖሬሽኑ መረጃ አመላክቷል።

ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *