የዓለም ነዳጅ ዋጋ ከአራት ወራት በኋላ ጭማሪ አሳየ

ጭማሪው የመጣው አሜሪካ በሩሲያ ነዳጅ ላይ አዲስ ማዕቀብ መጣሏን ተከትሎ ነው

ሩሲያ በየዕለቱ 700 ሺህ በርሜል ነዳጅ ለዓለም ገበያ በማቅረብ ላይ ነበረች

የዓለም ነዳጅ ዋጋ ከአራት ወራት በኋላ ጭማሪ አሳየ።

የሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት በዓለም ነዳጅ ግብይት ላይ ከፍተኛ የሚባል ተጽዕኖ ያደረሰ ሲሆን በየጊዜው ዋጋው እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል።

ላለፉት አራት ወራት ጭማሪ ያላሳየው የዓለም ነዳጅ ዋጋ አዲስ ጭማሪ ያሳየ ሲሆን አሜሪካ በሩሲያ ላይ ከሰሞኑ የጣለችው አዲስ ማዕቀብ ደግሞ ለነዳጅ ዋጋ መጨመር ዋነኛው ምክንያት ሆኗል።

ሮይተርስ እንደዘገበው ከሆነ አንድ ሊትር ድፍድፍ ነዳጅ በበርሜል ከነበረበት 77 ዶላር ወደ 80 ዶላር የገባ ሲሆን ይህም በአራት ወራት ውስጥ ትልቁ የዋጋ ጭማሪ ነው።

በየዕለቱ 700 ሺህ በርሜል ነዳጅ ለዓለም ገበያ በማቅረብ ላይ የነበረችው ሩሲያ በዩክሬን ጦርነት ምክንያት ማዕቀብ ተጥሎባታል።

አሜሪካ በሩሲያ ላይ አዲስ ማዕቀብ የጣለችው ነዳጅ መሸጧ ለጦርነቱ ዋነኛ ግብዓት ሆኗታል በሚል እና ነዳጇን ለዓለም ገበያ እንዳታቀርብ ለመከልከል በሚል ነው ተብሏል።

የነዳጅ ውጤቶችን የግብይት ስርዓት ለመደንገግ የወጣው አዋጅ ያስቀመጣቸው ቅጣቶች ምን ይመስላሉ

ይህን ተከትሎ የነዳጅ እጥረት ሊከሰት ይችላል የሚል ስጋት በነዳጅ ሸማች ሀገራት ላይ መፈጠሩን ተከትሎ መጠነኛ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል ተብሏል።

ይሁንና ሩሲያ እና ሸማች ሀገራት ይህን የአሜሪካ አዲስ ማዕቀብ ማምለጫ መንገዶችን መፈለጋቸው አይቀሬ እንደሚሆን የተገለጸ ሲሆን የነዳጅ ገበያው ላይ የዋጋ ጭማሪው ላይቀጥል እንደሚችል ተገልጿል።

ቻይና፣ ሕንድ እና ሌሎች በርካታ የዓለማችን ሀገራት የሩሲያን ነዳጅ በገፍ ከሚገዙ ሀገራት መካከል ዋነኞቹ ናቸው።

ምንጭ፦ አል አይን

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *