የካፒታል ገበያ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ገበያ መሪ ተዋናይ እንድትሆን ያስችላታል፤
ዘርፉ ሁሉንም በንቃት በማሳተፍ ምርትና አገልግሎቶችን በስፋት ማቅረብ ያስችላል፤
የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ በቴክኖሎጂ የሚታገዝ በመሆኑ ለሥራ እድል ፈጠራ እና ለኢኮኖሚ እድገት ገንቢ ሚና ይጫወታል፤
የባንኮችን ተቀማጭ ገንዘብ ለማሳደግ ወሳኝ ነው፤
የቁጠባ መጠንን ማሳደግና ፕራይቬታይዜሽንን ማጠናከር ለካፒታል ገበያ አስፈላጊ ናቸው፤
የሀገር ውስጥ ኢንቨስተሮች ገበያውን ከደገፉት በሀገር ውስጥ አቅም ኢኮኖሚውን ማጠናከር ያስችላል፤
ጠንካራ የካፒታል ገበያ መኖር በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆነ ኢኮኖሚ ለመገንባት ይረዳል፤
ትልቅ ትኩረት፤ ገበያውን የሚመራና የሚቆጣጣር ግልጽ የካፒታል ገበያ የህግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት ለካፒታል ገበያ ዕድገት ወሳኝ ነው፤
የካፒታል ገበያ ጥቅል የሀገርን ኢኮኖሚ የሚደግፍ እና የዜጎችን ህይወት የሚቀይር ዘርፍ ነው፤
የኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ንዋዮች ገበያ የተለያዩ የንግድ አይነቶችን ታሳቢ በማድረግ ሶስት የተለያዩ የገበያ አይነቶችን ማለትም የአክሲዮን ገበያ፣ የዕዳ ሰነድ ገበያ እና የአማራጭ ገበያን የሚያቀርብ ነው።
ምንጭ፦ ኢዜአ