የእስራኤል ባለሃብቶች በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ በእስራኤል የኢትዮጵያ አምባሳደር ተስፋዬ ይታይህ ጥሪ አቀረቡ።
በእስራኤል ለሚገኙ ባለሃብቶች በኢትዮጵያ ስላለው ኢንቨስትመንት የማስተዋወቂያ መርሃ ግብር የተካሄደ ሲሆን÷በዚሁ መርሐ ግብር ላይ ባለሃብቶች፣ የኩባንያ ሃላፊዎችና የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል
በመድረኩ አምባሳደር ተስፋዬ ÷ ኢትዮጵያ በግብርና፣ በአግሮ-ፕሮሰሲንግ፣ በኢንዱስትሪ ልማት፣ በማዕድን ማምረት እና በጤና ዘርፎች ያላትን ሰፊ የኢንቨስትመንት አማራጮች አብራርተዋል።
መንግስት ለኢንቨስትመንት ከሰጠው ትኩረት አኳያ በዘርፉ ስላሉ ማበረታቻዎች እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች በተለያዩ የልማት ኮሪደሮች ስለመገንባታቸው ገልጸዋል።
በመሆኑም ባለሃብቶቹ የተመቻቸውን የኢንቨስትመንት እድል በመጠቀም በኢትዮጵያ መዋዕለ ነዋያቸውን እንዲያፈሱ ጥሪ ማቅረባቸውን በእስራኤል ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ