የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮምሽን ከፓኪስታን ባለሃብቶች ጋር የኢንደስትሪ ፓርክ ልማት ፣ የፋርማሱቲካል እና የማሸጊያ ምርቶች አምራች ኢንደስትሪ ዘርፍ ላይ እንዲሳተፉ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡

የመግባቢያ ሰነዱን በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮምሽን ምክትል ኮምሽነር ዳንኤል ተሬሳ እና በፓኪስታን የባለሀብቶች ተወካይ የተፈረመ ሲሆን በኢትዮጵያ ለቀናት ቆይታ አድርጎ በሀገራችን እንዲሁም በአፍሪካ ገበያ ተሳታፊነቱን ለመጨመር እና ኢንቨስት ለማድረግ ፍላጎት ካሳየው የፓኪስታን የኢንቨስትመንት እና ንግድ ልዑክ ቡድን ጉብኝት አካል ነው፡፡

በፋርማሱቲካል ዘርፉ እና በማሸጊያ ምርቶች አምራች ኢንደስትሪ በቦሌ ለሚ እና ቂሊንጦ ኢንደስትሪያል ፓርኮች ለመግባት እና ለማልማት የአጭር ጊዜ ዕቅድ በባለሀብቶቹ እንደተያዘ የተገለፅ ሲሆን በተጨማሪም በ100 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ወጪ የኢትዮጵያ እና ፓኪስታን ወዳጅነት ኢንደስትሪያል ፓርክን ለመገንባት እና በተለያዩ አምራች ዘርፎች ኢንቨተሮችን ለመሳብ ዕቅድ እንዳለ ተጠቅሷል፡፡

ኮምሽነር ኢንጂነር ለሊሴ ነሜ በፊርማ ስነ ስርዓቱ መንግስት የፓኪስታን የኢንቨስትመንት ፍሰት በሀገራችን እንዲጨምር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ያረጋገጡ ሲሆን የተፈረመው የመግባቢያ ሰነድም በኮምሽኑ እና በፓኪስታን ኢንቨስተሮች መካከል ጠንካራ እና ረጅም ግንኙነት ለመመስረት ቁልፍ ሚና እንደሚጫወት ገልፅዋል፡፡

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *